ሮቤል ፍሊጶስ ለተመሰረተበት ክስ ጥፋተኛ አይደለሁም አለ

ሮቤል ፊሊጶስ እና ጠበቃው አቶ ደረጀ ደምሴ

በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነው የ 19 አመት እድሜ ወጣት ሮቤል ፍሊፖስ በቦስተን ማራቶን በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የሚጠረጠረው ዦኻር ሳርናየቭ ጓደኞች ከሆኑት ሁለት ሰዎች ጋር ቤቱ ውስጥ የገባ ቢሆንም አልገባሁም በማለት ለመርማሪዎች ዋሽቷል በሚል ተከሷል። እሱ ግን ጥፋተኛ አይደለሁም ብሏል። ሁለቱ ሰዎች ማስረጃን በመደበቅ ነው የተከሰሱት።

ስለጉዳዩ እንዲያብራሩልን አዳነች ፍሰሀየ የሱ ጠበቃ የሆኑትን አቶ ደረጀ ደምሴን አነጋግራለች። አቶ ደረጀ ስለክሱ በማብራራት ይጀመራሉ እንድታደምጡ እንጋብዛለን።

Your browser doesn’t support HTML5

Robel-Phillipos's-Case-9-16-13