የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም እና የብሪታኒያው ኦክስፈርድ ዩኒቨርስቲ ያወጡት ሪፖርት ሲሆን ከመካከላቸው ከግማሽ የሚበልጡት ሕጻናት መሆናቸውን አስታውቋል።
አርባ ከመቶ የሚሆኑት የሚኖሩት በጦርነት በሚታመሱ እና በአስተዳደር እና በምጣኔ ሀብት ደካማ በሆኑ ሀገሮች መሆኑን ሪፖርቱ ጠቁሟል።
የመንግሥታቱ ድርጅት ተቋም እና የኦክስፈርድ ዩኒቨርስቲው የድህነት እና የሰብዓዊ ዕድገት መርሐ ግብር ያወጡት የዘንድሮው ሪፖርት በጠቅላላው ስድስት ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ሕዝብ የሚኖርባቸው 112 ሀገሮችን መረጃ ያካተተ ነው።
በሪፖርቱ ሰንጠረዥ መሠረት በከፋ ድሕነት ከሚኖሩት 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሰዎች ውስጥ ግማሽ ገደማ የሚሆኑት የሚኖሩት በአምስት ሀገሮች እንደሆነ ተጠቁሟል። ህንድ 234 ሚሊዮን፥ ፓኪስታን 93 ሚሊዮን፥ ኢትዮጵያ 86 ሚሊዮን፥ ናይጄሪያ 74 ሚሊዮን እንዲሁም በኮንጎ 66 ሚሊዮን ሰዎች መሆናቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።