No media source currently available
አዲስ አበባ ጎጃም በረንዳ አካባቢን የሚያዘወትር ሰው ወጣቱን በጎ አድራጊ ዘካሪያስ ኪሮስን ያወቀዋል። ዘካሪያስ እጅ አጥሯቸው ጎዳና የወደቁትን ይመግባል፣ ለአረጋዊያን የንጽህና አገልግሎት ይሰጣል፥ የዘመመ ጎጃቸውን ይጠግናል። እሱ እና አጋሮቹ የሚያደርጓቸውን መልካም ግብሮች በማህበራዊ መገናኛዎች የሚያዩ ኢትዮጵያን የተቻለቸውን ይደግፋሉ። የተገኘውን ይዞ ዘካሪያስ ርዳታ ወደ ሚያስፈልጋቸው ወገኖች ቤት ይመላለሳል።