በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዮናስ ቢሆነኝ - ‘ያልተዘፈነለት ጀግና’

ዮናስ ቢሆነኝ
ዮናስ ቢሆነኝ

ዮናስ ቢሆነኝ በምዕራባዊ አሜሪካይቱ ዋሺንግተን ግዛት ሲያትል ከተማ ውስጥ የመኪና መጠገኛ ጋራዥ አለው። ይሄ በራሱ አንድ ስኬት ነው። በባዕድ አገር የራስን ድርጅት አቋቁሞ የሥራ ባለቤት፣ የሥራ ፈጣሪ መሆንና፣ ለሌሎችም መትረፍ!

please wait

No media source currently available

0:00 0:10:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዮናስ ቢሆነኝ በምዕራባዊ አሜሪካይቱ ዋሺንግተን ግዛት ሲያትል ከተማ ውስጥ የመኪና መጠገኛ ጋራዥ አለው። ይሄ በራሱ አንድ ስኬት ነው። በባዕድ አገር የራስን ድርጅት አቋቁሞ የሥራ ባለቤት፣ የሥራ ፈጣሪ መሆንና፣ ለሌሎችም መትረፍ!

ከዚያ ሌላ የዮናስ ሥራ ጋራዥ ውስጥ ብቻ አይወሰንም። ማኅረሰቡን በተለያዩ ሁኔታዎች ያገለግላል። ለምሳሌም ስብሰባዎችን ማዘጋጀት፣ በስብሰባዎች ሥፍራ የመድረኩን መነጋገሪያና የድምፅ መሣሪያዎች ማስተካከል ወይም ማዘጋጀት፣ ለማኅበረሰቡ የሚሆን ዕርዳታ በሚካሄድበት ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝቶ መርዳት፣ መካኒክ ለመሆን ፍላጎት ያላቸውን ወጣት ኢትዮጵያውያን በነፃ ማሠልጠን!! እነዚህ ሁሉ በጎ ጎኖች፣ ዮናስን፣ በማኀረሰቡ ውስጥ መልአክ አሰኝተውታል» ይላል “ኢትዮሚድያ” በሚባለው ዌብሣይት ላይ የወጣ ፅሁፍ፡፡

ቪኦኤ ዮናስ ቢሆነኝን በ “ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ” ዝግጅቱ ለአየር አብቅቶታል፡፡

ለሙሉው ታሪክ የአዲሱ አበበን ዘገባ የያዘውን የድምፅ ፋይል ከፍተው ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG