በአውሮፓ አቆጣጠር የያዝነው 2013 ዓ.ም “ዓለምአቀፍ የውኃ ትብብር ዓመት” ሆኖ እንዲያልፍ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በታኅሣስ 2003 ዓ.ም ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔው ወስኖ ነበር፡፡
አቶ ብዙነህ ቶልቻ - የኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር
የዓመቱ ዘመቻ እንዲቀናጅና እንዲመራ የተደረገው ባለው ዘርፈብዙ ገፅታና ባርይ የተፈጥሮና ማኅበራዊ ሣይንሶችን፣ ትምህርትን፣ ባሕልና መገናኛን አጣምሮ የያዘ በመሆኑ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሣይንስና የባሕል ድርጅት - ዩኔስኮ ነው፡፡
መጋቢት 13 ቀን ዓለምአቀፍ የውኃ ቀን እንዲሆን ሃሣቡ የቀረበው እአአ በ1992 ዓ.ም ሪዮ ዴ ጃኔይሮ ላይ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የተፈጥሮ አካባቢ እና የልማት ጉባዔ ላይ ነበር፡፡
ያንን ጉባዔ ተከትሎ የተጠራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ መጋቢት 13 የውኃ ቀን ሆና እንዲውል ወስኖ የመጀመሪያው ዕለት በአውሮፓ አቀጣጠር በ1993 ዓ.ም - በዓመቱ ማለት ነው - ተከበረ፡፡
የመንግሥታቱ ድርጅት ውሣኔውን ያሣለፈውና ዕለቱም እንዲከበር የወሰነው የሪዮው ጉባዔ በ21ኛው አጀንዳው ላይ ያስቀመጠው “ለሰው ልጅ የለት ተዕለት ሕይወት ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለውን ውኃ ወይም ፍሬሽ ወተር አስፈላጊነት ለማጉላት ነው፡፡”
መንግሥታት ዕቱን ከየራሣቸው ተጨባጭ ሁኔታና አስፈላጊነት ጋር እያጣመሩ የግንዛቤ ማስጨበጫና የዕውቀት ማዳበሪያ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ እንዲያከብሩት ነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚያሣስበው፡፡
ኢትዮጵያ 123 ቢሊዮን ሜትር ኩብ የገፀ-ምድር እና እስከ 40 ቢሊዮን ሜትር ኩብ የሚደርስ የከርሠ-ምድር ውኃ፣ ወደ 5.3 ሚሊየን ሄክታር በመስኖ ሊለማ የሚችል መሬት እንዳላት የኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
የዓለም የውኃ ቀን - መጋቢት 13
በመስኖ ሊለማ ከሚችለው መሬት ውስጥ በእርሣቸው መሥሪያ ቤት ክትትል በሚደረግበት በመካከለኛና ሰፋፊ መስኖ ልማት ከ210 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ እየለማ መሆኑንና የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መጠናቀቂያ ይሆናል ተብሎ በሚጠበቀው በ2007 ዓ.ም ደግሞ ይህ ስፋት ከ750 ሺህ ሄክታር በላይ እንደሚደርስ አቶ ብዙነህ አመልክተዋል፡፡የንፁህ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ አቶ ብዙነህ ሲናገሩ “በአሁኑ ጊዜ ከ78 ከመቶ በላይ የሚሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ የንፁህ ውኃ ተጠቃሚ ነው” ብለዋል፡፡
ዘገባውን ያዳምጡ፡፡