በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤጊ እና ቆንዳላ ወረዳዎች በቀጠለ ግጭት ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ


በቤጊ እና ቆንዳላ ወረዳዎች በቀጠለ ግጭት ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:17 0:00

በምዕራብ ወለጋ ዞን በቤጊ እና በቆንዳላ ወረዳዎች፣ በመንግሥት ታጣቂዎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል፣ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ባገረሸው ግጭት፣ ቢያንስ ሦስት ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ከአፈገፈጉ በኋላ የመንግሥት ኀይሎች በወሰዱት ርምጃ ሰዎቹ መገደላቸውን የገለጹት የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች፣ “ከሕግ አግባብ ውጪ ነው” ሲሉ ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኀይሉ አዱኛ ግን፣ “የመንግሥት ኀይሎች ሲቪል ሰዎችን ዒላማ አያደርጉም፤” በማለት ውንጀላውን አስተባብለዋል።

ለታጣቂው ቡድን የሎጅስቲክስ ድጋፍ የሚያደርጉና መረጃ የሚሰጡ ሰዎችም እንደሚያዙ አክለው የገለጹት አቶ ኀይሉ፣ ጉዳያቸው የሚጣራው “ሕግን በተከተለ መንገድ” መኾኑን ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG