በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ ተፈናቃዮች ዛሬም ድጋፍ ጥበቃ ላይ ነን አሉ


የሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ ተፈናቃዮች ዛሬም ድጋፍ ጥበቃ ላይ ነን አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:54 0:00

ከኦሮምያ ክልል ሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች ውስጥ በጸጥታ ችግር ተፈናቅለው በአሙሩ ወረዳ አገምሳ ከተማና ኪረሙ ወረዳ ውስጥ በተለያዩ ስፍራዎች መጠለላቸውን የሚናገሩ ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበላቸው እንዳልሆነ አስታወቁ። መንግሥት በአስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው እነዚሁ ተፈናቃዮች ጠይቀዋል፡፡

ከሁለት የወለጋ ዞኖች የተፈናቀሉ ከ178ሺ በላይ ሰዎች በተለያዩ መጠለያዎችና ዘመድ ጋር ተጠግተው እንደሚገኙ የገለጸው የኦሮምያ የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ሥራ አመራር ኮሚሽን ወደ ነቀምቴ ከተማ እህል ማድረሱን እና ድጋፉን የፀጥታ ችግር ወዳለባቸው አካባቢዎች እያጓጓዘ እንደሚገኝ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG