ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በኮሎምቢያ ዪንቨርስቲ(ኒው ዮርክ) ተገኝተው ስለ አለም ምጣኔ ሃብት ቀውስና የአፍሪቃ ሀገሮች ከቀውሱ የሚላቀቁበትን መንገድ አስመልክቶ ለተማሪዎች ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢሕአዴግ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ከተለያዩ የአሜሪካ ክፍላተ-ሀገር በቦታው ተገኝተው፤ ድጋፍና ወቀሳቸውን እያሰሙ ነው፡፡ ኒው ዮርክ ፖሊስም በሁለቱ ወገኖች መካከል የከፋ ግጭት እንዳይፈጠር ነጣጥሏቸዋል፡፡ ሄኖክ ሰማእግዜር በቦታው ተገኝቶ የዘገበውን ያድምጡ፡፡