የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ትላንት ማክሰኞ የእስራኤልን ፕሬዝዳንት አስተናግደዋል። ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕም ከእስራኤሉ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋራ የተለያዩ የስልክ ጥሪዎችን አድርገዋል። ባንድ ወቅት የተካሄዱ እነዚህ ሁለት ንግግሮች በጋዛ እና ሊባኖስ ግጭቶች ላይ ያተኮሩ ሲሆን በሃማስ የተያዙ ታጋቾች እንደሚፈቱ ተስፋ አድርገዋል። የቪኦኤው የኋይት ሃውስ ዘጋቢ አኒታ ፓወል ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።