በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቆይታ ከመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ሴት የንግግር ልቀት ተሸላሚ ጋር


ቆይታ ከመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ሴት የንግግር ልቀት ተሸላሚ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:43 0:00

ወጣቶች ስኬታማ እንዲሆኑ ከሚያደርጓቸው ነገሮች አንዱ ሃሳብን በጥራት መግለጽ መቻል ነው፡፡ የንግግር ክህሎትን ማዳበር የተሻለ ስራም ሆነ የትምህርት ዕድል መጎናጸፍን ጨምሮ ወደ አመራር ደረጃ ለማደግም ያግዛል፡፡ በአለም ዙሪያ ሰዎች ይህንን ክህሎት እንዲያዳብሩ ከሚረዱ ተቋሞች መሃከል አንዱ የሆነው ቶስ ማስተር ኢንተርናሽናል ሲሆን ይሄ ተቋም በኢትዮጵያ መንቀሳቀሰ ከጀመረ ሶስት አስርት አመታትን አስቆጥሯል፡፡

ተቋሙ ወጣቶች የንግግር እና የአመራር ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ፣ የእንግሊዘኛ ቋንቋቸውን እንዲያሻሽሉ እና በተለያዩ የሙያ እና የእድሜ ደረጃ ላይ ካሉ ሰዎች ጋር እንዲተሳሰሩ ያግዛል፡፡ኢትዮጲስ የቡድኑ የቀድሞ ዳይሬክተር እና የአሁን አባል ስትሆን በላቀ የንግግር ክህሎታቸው አለም አቀፍ እውቅና ከተሰጣቸው አራት ኢትዮጵያዊያን መሃከል አንዷ እንዲሁም ደግሞ የቶስማስተር የምስራቅ አፍሪካ በእድሜ ወጣቷ ተሸላሚም ናት፡፡ ኢትዮጲስ ታደሰ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡

(ሙሉ ቃለመጠይቁን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ)

XS
SM
MD
LG