በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጤናማ የእናትነት ወር በኢትዮጵያ


ጤናማ የእናትነት ወር በኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:47 0:00

ጤናማ የእናትነት ወር በመላው ዓለም ከጥር ወር መግቢያ አንስቶ እየታሰበ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያም “መከላከል በምንችላቸው ምክንያቶች የሚከሰቱ የእናቶችን ሞት በጋራ እንግታ”! በሚል መሪ ቃል እየታሰበ ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2017 በተባበሩት መንግስታት በወጣው ሪፖርት መሰረት በየዓመቱ በአለማችን ወደ 300 ሺ የሚደርሱ እናቶች ከእርግዝና፣ ወሊድና ድህረ ወሊድ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ህይወታቸውን እንደሚያጡ አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያም በዓመት ወደ 14 ሺህ በአመት በየቀኑ ደግሞ ወደ 38 የሚሆኑ እናቶች ከእርግዝና ጋር በተያያዘ በሚከሰቱ የጤና ችግሮች ህይወታቸውን እንደሚያጡ የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት እያስተናገደችው ባለቻቸው ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ እክሎች ምክንያት እየተሻሻለ የነበረው የእናቶች ጤና እንክብካቤ እያሽቆለቆለ እንደሄደ ባለሞያዎች ይናገራሉ።

ለመሆኑ ጤናማ እናትነት ምን ማለት ነው? በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የጽንስ እና የማህጸን ሬዚደንት ሃኪም ዶ/ር አህመድ አደም መልስ አላቸው።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG