የሥራ ፈጣሪ ማኅበረሰቡ፣ በንግዱ ዘርፍ ትስስርን በመፍጠር እና በመረዳዳት አዎንታዊ ተጽእኖ ማሳደር የሚችል ማኅበረሰብን የመገንባት ሕልም ይዞ እየሠራ ይገኛል፡፡ በመላው ኢትዮጵያ በጎ ተጽእኖውን ለማስፋፋት አልሞ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው “ዘ ዲስረፕተርስ ዴን”፣በአሁኑ ወቅት፣ በአዳማ እና በሐዋሳ ከተሞች ሥራ ለመጀመር ሲዘጋጅ፣ በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ካሉ ኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች ጋራም ለመቀናጀት በመነጋገር ላይ ነው፡፡
አጋር መሥራቾቹ፣ ዶር. ታምራት ሱልጣንና አቤኔዘር ባዬ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርገዋል፡፡ ኤደን ገረመው ነች ያነጋገረቻቸው።