No media source currently available
ኒው ዮርክ ከተማ ላይ የሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከዓመቱ ትልልቅ ስብስቦች መካከል አንዱ ነው። ስለሆነም የጉባኤው ተሳታፊዎችን ደኅንነት ለመጠብቅ ሲባል ከባድ የጥበቃ ተግባር ማካሄድ ግድ ይል ነበር። በያዝነው ዓመት ግን የዓለም ሃገሮች መሪዎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጉባኤያቸውን በቨርቿል ወይም በርቀት ለማካሄድ ወስነዋል።