በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአንተኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉዞና የትንታኔ ባለሞያ አስተያየት


የአንተኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉዞና የትንታኔ ባለሞያ አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:59 0:00

ካለፈው ሰኞ አንስቶ ለአምስት ቀናት የአፍሪካ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ያለፉትን ሁለት ቀናት የኬኒያ ቆይታቸውን አገባደው በምዕራብ አፍሪካዊያን ሃገራት ናይጄሪያና ሴኒጋል ለሚያደርጉት ቆይታ አቡጃ ገብተዋል።

በኬንያ ቆይታቸው የኢትዮጵያን ጉዳይ ጨምሮ ቀጠናዊ ጸጥታን እና ሰላምን፣ ኮቪድ 19’ን እና እንዲሁም የዓየር ንብረትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከፕሬዘዳንት አሁሩ ኬኒያታ እና ከኬኒያ ከፍተኛ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዛሬ በአቡጃ ቆይታቸው ከናይጄሪያው ፕሬዘዳንት ሞሃማዱ ቡሃሪ፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚ ኦሲንባጆ እና ከሌሎች የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣንት ጋር ይወያያሉ ተብሏል።

በናይጄሪያ ቆይታቸውም ዴሞክራሲን፣ የዓየር ንብረት ለውጥን እና ኮቪድ 19’ን በሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር በተጨማሪም የፕሬዘዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በአፍሪካ ላይ ያለውን ፖሊሲ የተመለከተ ንግግር እንደሚያሰሙም ይጠበቃል፡፡

ከዚሁ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተንኒ ብሊንከን የኬኒያ ቆይታ ምን እንደሚሚስል ከባለሞያ ትንታኔ ጋር ተዘገቧል፡፡

// ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡት//

XS
SM
MD
LG