የትረምፕ አስተዳደር የታጋቾች ተደራዳሪ በቅርቡ በአሜሪካ ከተሰየመው የሽብር ቡድን ሐማስ ተወካዮች ጋር ያደረጉትን ንግግር “ጠቃሚ” ብለውታል።
ንግግሩ በሐማስ ተይዞ የነበረውን አሜሪካዊ-እስራኤላዊን በመልቀቅ ላይ ያተኮረ ነበር። ንግግሩ የተካሄደው እስራኤል በዚህ ሳምንት የተኩስ አቁም ድርድር ላይ ለመወያየት የልዑካን ቡድን ልታሰማራ እንደሆነ በገለጸችበት ወቅት ነው፡፡
የቪኦኤ አራሽ አራብሳዲ የላከቸውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።