ዋሺንግተን ዲሲ —
አፍሪካ ተለዋዋጭ በሆነው የአየር ንብረት ሁኔታ ውስጥ ቻይ ሆና እንድትዘልቅና በምግብ እራሷን እንድትችል አንድም ሌሎች በአፍሪካ ሊያምኑ እንደሚገባ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የአህጉሪቱን ቁርጠኝነት ወደተግባር ለመለወጥ የአሜሪካ ድጋፍ እንዲሰፋ ተጠይቋል፡፡
እነዚህ ሃሣቦች በተነሱበት በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጋባዥነትና አስተናጋጅነት በተካሄደው የአፍሪካ - ዩናይትድ ስቴትስ የመሪዎች ስብሰባ ላይ በተሰናዳው የአፍሪካ ተለማጭነት ወይም የተፈጥሮ አካባቢና የአየር ንብረት መለዋወጥ ቻይነትና የምግብ ዋስትና መድረክ ላይ መክሯል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አፍሪካና ዩናይትድ ስቴትስ ተባብረው በመሥራታቸው በያዝነው የአውሮፓ ዓመት የውጭ መዋዕለ ነዋይ ፍሰቱ ሰማንያ ቢልዮን ዶላር መድረሱ ተገልጿል፡፡
በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘውን የውጭ ኢንቭስትመንት የአሜሪካ ኩባንያዎች በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡
በጉባዔው ላይ የተገኙት አፍሪካዊያኑ መሪዎች ከአፍሪካ የንግድ ድርጅቶች መሪዎችና ከዩናይትድ ስቴትስ ኩባንያዎች ጋር በምጣኔ ኃብቱ ዙሪያ መክረዋል፡፡
ለዝርዝሩ በተያያዘው የድምፅ ፋይል ውስጥ የተካተቱትን ዘገባዎች ያዳምጡ፡፡