በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለሳዑዲ የምታቀርበውን የመሣሪያ ሽያጭ ልታቋርጥ ዝግጅት ላይ ነች


አሜሪካ ለሳዑዲ የምታቀርበውን የመሣሪያ ሽያጭ ልታቋርጥ ዝግጅት ላይ ነች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:35 0:00

ሳዑዲ አረቢያ ከሩሲያ ጋር በመወገን ባለፈው ሳምንት በተደረገው ‘OPEC+’ በተሰኘው የነዳጅ ላኪ ሃገሮች ስብስባ ላይ ለዓለም የሚቀርበው የነዳጅ ምርት መጠን እንዲቀነስ መወሰኗን፣ ለሳዑዲ አረቢያ የሚደረገውን የመሣሪያ ሽያጭ ለማቋረጥ የሚያስችል ረቂቅ ሕግ በማዘጋጀት ላይ ናቸው።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዋሽንግተን ከሪያድ ጋር ያላትን ግኑኝነት እንደገና ለመገምገም ከም/ቤቱ ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ዋይት ኃውስ አስታውቋል።

“ኦፔክ ሲደመር አንድ” የተሰኘው የነዳጅ ላኪ ሀገሮች ስብስብ ባለፈው ሳምንት የነዳጅ ዘይት ምርቱን በ2 ሚሊዮን በርሜል ለመቀነስ ወስኗል። ውሳኔው አሜሪካ ተቃውሞዋን እያሰማች የተፈፀመ በመሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ አውጪዎች የነዳጅ ላኪዎቹ ማኅበር መሪ ለሆነችው ለሳዑዲ አረቢያ ቆንጠጥ የሚያደርግ ቅጣት እንዲሰጣት እየጠየቁ ነው።

“ኦፔክ ሲደመር አንድ” የተባለው ቡድን 23 ነዳጅ ላኪ ሀገራት አባል የሆኑበት ስብስብ ሲሆን ምን ያህል ነዳጅ ዘይት ለዓለም ገበያ መቅረብ እንዳለበት ይወስናል። ሩሲያ አንዷ አባል ሀገር ስትሆን አሜሪካ አይደለችም።

የአሜሪካ ም/ቤት አባላት በሚቀጥለው ወር ከምርጫ መልስ ወደ ዋሽንግተን ሲመለሱ፣ ጉዳዩን በተመለክተ ተቀራርበው እንደሚሠሩ ፕሬዚንት ጆ ባይደን ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG