በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካውያን ዕጩዎች በአሜሪካ ምርጫዎች


በዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ በመካሄድ ላይ ያለው ምርጫ፣ በሁለት ፕሬዚዳንቶች መካከል የሚደረገው ፉክክር ከፍተኛ ግምት ይሰጠው እንጂ፣ ሁለቱንም ምክር ቤቶች ጨምሮ በየደረጃው ባሉት ምክር ቤቶችም የተወካዮች የምርጫ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካከል በኔቫዳ ላስ ቬጋስ አሌክዛንደር አሰፋ በድጋሚ 42ኛው ድስትሪክት በመወከል ለዴሞክራቲክ ፓርቲ ይወዳዳራሉ፡፡ ሳምራ ብሩክ በኒው ዮርክ አልባኒ 55ኛው ዲስትሪክት ምክር ቤት አባልነት ለመወዳደር ቀርበዋል፡፡ ኢትዮጵያዊት አሜሪካዊው ጀሚላ ማሜ ለሴንት ፖል ሚኒሶታ ትምህርት ቤት ቦርድ ይወዳደራሉ፡፡ ከትውልደ ኤርትራውያንም እንዲሁ ሜሮን ስመዳር ለኦክላንድ ከተማ ምክር ቤት ካውንስል እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡

የተለያየ አመለካከት ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ምርጫው ማምጣት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ዕጪ ፖለቲከኞች ፍላጎትና የዘወትር ፈተና ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ የቪኦኤ ዘጋቢ ኬሮል ገንስበርግ እንደዘገበችው እየተቀየረ ያለው የአሜሪካ ማህበረሰብ ስብጥር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ የማህበረሰብ አባላትን በዕጩነት መልምለው ወደ ፓርቲያቸው እንዲያመጡ ግፊት ያሳደረባቸው ይመስላል፡፡

ይህ አዳዲስ አሜሪካውያን ዜጎችንም ይጨምራል፡፡ ከፋይር ኃውስ ስትራቴጂ የሪፐብሊካን ስትራቴጂስት አሌክስ ካነንት እንዲህ ይላሉ

“ይህ ነገር ሪፐብክሊካን ፓርቲን ጨምሮ ለሁለቱም ፓርቲዎች ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ ሁኖ ለረጀም ጊዜ ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ በ2008 የሪፐብሊካን ብሄራዊ ኮሚቴ የፕሬስ ሰክሬታሪ ነበርኩ፡፡ ያን ጊዜ ቅድሚያ የተሰጠው ነገር ነበር፡፡ ዛሬም እንዲሁ ቅድሚያ የተሰጠው ነገር ነው፡፡ ይህ ፓርቲያችን ሊያደርገው የሚሞክረው አንድ ነገር ነው፡፡ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ አጠንክረን እንደምናደርገው ይመስለኛል፡፡ በጣም ትልቅና የተደባለቅን አገር ነን፡፡ ምርጫውን ለማሸነፍ ከተፈለገ ከማህበረሰቡ የመጣ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ምርጫውን የሚመርጠውም እሱ ነው፡፡ ስለዚህ ያ ጥቁር እጩዎችንም መመልመልን ይጨምራል፡፡”

ግን ችግሩ ተስፋ ያላቸው ፖለቲከኞች ለምርጫው ውድድር የሚቀርቡት እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ ለምሳሌ ከአራት ዓመት በፊት፣ ዳቪሻ ጆንሰን፣ የ መጀመሪያ የሁለተኛና ሶስተኛ ትውልድ የሆኑ አፍሪካ አሜሪካውያንን የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎች የሚያማክር የአማካሪ ድርጅት በአትላንታ ጆርጂያ አቋቁመው ነበር፡፡ እንዲህ ይላሉ ስለልምዳቸው

ድርጅቴን በጊነት ካውንቲ በማቋቋም ነው የጀመርኩት፡፡ ብዙ አፍሪካውያን በዚያ ይገኛሉ፡፡ እነሱ በፖለቲካው ምክር ወይም ሥልጠና የሚያገኙበትን፣ የሚማሩበትን፣ እድሎችና ሁኔታዎችን ማመቻቸት የሚያስፈልግ መሆኑን ተገንዘብኩ፡፡ ስለዚህ እኔ ራሴ የፖለቲካ ስልጠና ወደሚሰጡ የተለያዩ ተቋማት በመሄድ በፖለቲካው ዓለም በመግባትና በምርጫውም ሂደት ለመሳተፍ ምን ምን እውቅትና ሥልጠናዎችን እንደሚያስፈልጉ መማር ቻልኩ፡፡ ከዚያም ልምዱ ካላቸው ሰዎች በቀጥታ ብዙ ነገር አገኘሁ፡፡

ስልጠና በጣም አስፈላጊ ነገር መሆኑን፣ በኮላራዶ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ናኩዬታ ሪክስ ይስማማሉ፡፡ ከተለያዩ ድርጅቶች የምክር እርዳታ እንዳገኙ ይናገራሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ኒው አሜሪካን ሊደርስ የሚለውና እያደገ የሚገኘው ገለልተኛ ተቋም አንዱ ሲሆን የዴሞክራቲ ፓርቲ የሚወዳደሩ ሴቶችን በማነጽ ያዘጋጃል፡፡ ሪክስ እንዲህ ይላሉ

“እንዴት አድርገን ገንዘብ ማሰባሰብ እንደምንችል አስተማሩን፡፡ ራሳችንን እንዴት አድርገን መግለጽ እንደምንችል፣ የሚደመጥ ድንቅ ንግግር እንዴት አድርገን ማሰማት እንደምንችል አሰለጠኑን፡፡ ስለዚህ እነዚህ ነገሮች በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት እንድሰጠው ያደርገናል፣ ሰዎችም ያደምጡናል፡፡”

ሪክስ በላይቤሪያ የተነሳውን ወታደራዊ መፈንቀለ መንግሥት ተከትሎ የተነሳውን አመጽ ሸሽተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ አሜሪካ ሲመጡ ገና ታዳጊ ሴት ልጅ ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን እንደ አንስተኛ ንግድ ባለቤት፣ ልጇን ብቻዋን እንደምታሳድግ ስደተኛ እናት በመሆን በዴንቨር አሮራ አካባቢ ያሉ ተመሳሳይ ሴቶች ድምጽ ለመሆን እጩ ሆነው ከምርጫው ሜዳ ወጥተዋል፡፡ እንዲህ ብለዋል ሪክስ፣

“በጣም የተየቀያየጠ ማህበረሰብ ነው፡፡ ከአምስት ሰው አንዱ ከሌላ አገር የመጣ መሆኑን ይናገራል፡፡ ከቻይና ይሁን በርማ ወይም ደቡብ አሜሪካ ሆነ አፍሪካ፣ ልዩነት የለውም ብቻ ሁላችንም ከሁሉም ቦታዎች ነው የመጣነው፡፡”

ለዩናይትድ ስቴት አዲስ ፊት የሆኑ አዲስ መጥ እጩዎች የምርጫ ዘመቻ ሲያካሄዱ በአንጻራዊነት መንገዱ አቀበት እንደሚሆንባቸው መገመት ይቻላል፡፡

“የአፍሪካውያን አንዱ ጥንካሬ የህዝብ ኃይል አላቸው፡፡ ከገንዘብ ውጭ ያለው አንዱ ነገር የህዝብ ድጋፍ ነው፡፡ ያ ድጋፍ ከዩናይትድ ስቴት ስ ብቻ የሚገኝ ላይሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ አገር ቤት አፍሪካ ያሉ ሰዎች “ስማ ሜሪላንድ የሚኖር አንድ የአጎቴ ልጅ አለ ቴክሳስ እማውቃቸው ሰዎች አሉ ይላሉ፡፡ ስለዚህ ካደገው የስልክህ ቋት ተጨማሪ ሰዎችን አገኘህ ማለት ነው፡፡ አሁን ስላንተ ሆነው የቴክስት መልዕክት የሚልኩ ሰዎች ይኖሩሃል፡፡ ያ ማለት በምርጫውም ቀን ድምጽ ሊሰጡ የሚወጡ ሰዎች አሉህ ማለት ነው፡፡”

በምርጫው ቀን ውጤቱ ምንም ይሁን ምን፣ የፖለቲካ ሥልጣን የመያዝ ፍላጎት መኖሩ በራሱ ለወደፊቱ ምርጫ የሚረዳ ይሆናል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

አፍሪካውያን ዕጩዎች በአሜሪካ ምርጫዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:03 0:00


XS
SM
MD
LG