በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አዲስ አባላት


የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት /የሎጎ ሥዕል ከፋይል የተገኘ/
የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት /የሎጎ ሥዕል ከፋይል የተገኘ/

በሰብዓዊ መብቶች አያያዛቸው ላይ ጥያቄ ያለባቸው ሃገሮች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ተደርገዋል ሲሉ የመብቶች ተሟጋች ቡድኖች ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡





please wait

No media source currently available

0:00 0:06:29 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት /የሎጎ ሥዕል ከፋይል የተገኘ/
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት /የሎጎ ሥዕል ከፋይል የተገኘ/

መቀመጫው ጄኔቫ ለሆነው ምክር ቤት ትናንት ከተመረጡት አሥራ ስምንት ሃገሮች ብቃት ያላቸውና መመዘኛውን የሚያሟሉት አንድ ሦስተኛ ብቻ መሆናቸውን የመብቶች ተሟጋቾቹ ገልፀዋል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዋች ከተመረጡት ሃገሮች መካከል ኢትዮጵያን አንስቶ በሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ከሚታወቁ ሃገሮች አንዷ እንደሆነች አመልክቷል፡፡
አርባ ሰባት መቀመጫዎች ያሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አዘውትሮ የሚወቅሰው ለእሥራኤል ጉዳይ ልዩ ትኩረት ይሰጣል እየተባለ ነው፡፡ ከዚያ ጋር በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ታሪካቸው ላይ እድፍ ብጤ አይጠፋቸውም የሚባሉ ሃገሮች አባላቱ የመሆናቸው ጉዳይም ሌላው ነቀፌታ የሚያደርስበት ነጥብ ነው፡፡ በምክር ቤቱ ውስጥ ያሉት መቀመጫዎች የሚደለደሉት በአካባቢያዊ የአመዳደብና የውክልና ሥርዓት ነው፡፡

በዘንድሮው የምክር ቤቱ አባላት አሰያየም ላይ እውነተኛ ፉክክር የተካሄደው ከአምስት መቀመጫዎቹ ሦስቱን እንዲሞላ በተጠየቀውን “የምዕራብና ሌሎች” በሚባለው ምድብ ውስጥ ነው፡፡

ለቦታዎቹ ከተፎካከሩት አምስት ሃገሮች አየርላንድ፣ ጀርመን እና ዩናይትድ ስቴትስ ግሪክንና ስዊድንን አሸንፈው ገብተዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ቀደም ባሉ ዓመታት የምክር ቤቱ አባል ያለመሆን አቋም ይዛ ቆይታ የነበረ ቢሆንም ይህንን ትናንት ያሸነፈችበትን መቀመጫ የያዘችው የቀድሞ አቋሟን ቀይራ በ2009 ዓ.ም አባል ከሆነች ወዲህ ነበር፡፡ በትናንቱ ምርጫ ለሁለተኛ ተከታታይ ዘመን ማሸነፏ ነው፡፡

ዋሽንግተን የምክር ቤቱ አባል መሆኗ የተለየ ገፅታን የሚያላብሣት መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አምባሣደሯ ሱዛን ራይስ ጠቁመው በአባልነቷ በመቀጠልም ምክር ቤቱን እንደምታጠናክር ገልፀዋል፡፡
ሱዛን ራይስ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሣደር
ሱዛን ራይስ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሣደር

“በ2009 ዓ.ም የምክር ቤቱ አባል ለመሆን የወሰንነው ዩናይትድ ስቴትስ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣን ለመቃወም ግንባር ቀደም መሆን ያለባት በመሆኑና በዓለማችን እጅግ ጨካኝ በሆኑ አገዛዞች ተጨምድደው እየኖሩና እየተሰቃዩ ላሉ ሕዝቦች ቤዛ ሆነን መጮኽ አለብን ከሚል ዕምነታችን በመነሣት ነው” ብለዋል ራይስ፡፡

የሌሎች አሸናፊዎች ምርጫ የተወሰነው በየክልላቸው ምድቦች ውስጥ ቀደም ሲል በተከናወኑ አካሄዶች ሲሆን በምክር ቤቱ ውስጥ ያሉ ባዶ መቀመጫዎቻቸውን ለመሙላት የሚያስችላቸውን ውክልና ነው የሰጡት፡፡
የአፍሪካን አምስቱን ባዶ መቀመጫቻዎች የሚሞሉት አይቮሪ ኮስት፣ ኢትዮጵያ፣ ጋቦን፣ ኬንያ እና ሴየራ ሌዖን ናቸው፡፡

የእሥያና የፓሲፊክ ሃገሮች ምድብም እንዲሁ አምስት መቀመጫዎቹን ለመሙላት ያቀረባቸው ጃፓንን፣ ካዛኽስታንን፣ ደቡብ ኮርያን፣ ፓኪስታንና የተባበሩት ዐረብ ኤሚሬቶችን ነው፡፡

ኢስቶንያና ሞንቴኔግሮ ሁለቱን የምሥራቅ አውሮፓ፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል እና ቬኔዝዌላ ደግሞ ሦስቱን የላቲን አሜሪካና ካሪቢያን ባዶ መቀመጫቻች ይይዛሉ፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዋች


ከእነዚህ ሃገሮች ቢያንስ ሰባቱ በሰብዓዊ መብቶች አያያዛቸው እራሣቸው ጥያቄ ያለባቸው መሆኑን የመብቶች ተሟጋች ቡድኖች ይናገራሉ፡፡
እነዚህ ሃገሮች አይቮሪ ኮስት፣ ኢትዮጵያ፣ ጋቦን፣ ካዛኽስታን፣ ፓኪስታን፣ የተባበሩት የዐረብ ኤሚሬቶች እና ቬኔዝዌላ ናቸው፡፡

ፊሊፕ ቦሎፒዮን፤ በሂዩማን ራይትስ ዋች የተባበሩት መንግሥታት ጉዳዮች ዳይሬክተር


የሂዩማን ራይትስ ዋች የተባበሩት መንግሥታት ዳይሬክተር ፊሊፕ ቦሎፒዮን የምክርቤቱ አባል ለመሆን ፉክክር ያለመኖሩና የሰብዓዊ ለመብቶች አያያዛቸው ጥያቄ ውስጥ የሆነ ሃገሮች አባል የመሆናቸው ጉዳይ ቅሬታን የሚያስነሣ መሆኑን በመጥቀስ ነቅፈዋል፡፡

ቦሎፒዮን የኢትዮጵያን የመብቶች አያያዝ ታሪክ አንስተውም ወቅሰዋል፡፡

“የኢትዮጵያ መንግሥት - አሉ ቦሎፒዮን - ይህንን አጋጣሚ ትርጉም ያላቸውን እርምጃዎች ለመውሰድ ሊጠቀምበት ይገባል፡፡ ለምሣሌ ሃሣብን በመግለፅና በመሰብሰብ ነፃነት፣ ወይም የፀጥታ ኃይሎቹን በተጠያቂነት በመያዝ፣ በተጨማሪም ምናልባትም አሁን እየተቀላቀለው ካለው የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጋር በእውነተኝነት መተባበር መጀመር አለበት፡፡”
ዳንኤል በቀለ፤ በሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ዳይሬክተር
ዳንኤል በቀለ፤ በሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ዳይሬክተር

በሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል በቀለም ለቪኦኤ ተመሣሣይ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

አዲሶቹ የምክር ቤቱ አባል ሃገሮች ለሦስት ዓመት የሚዘልቀውን አባልነታቸውን የሚጀምሩት በመጭው የአውሮፓዊያን ዓመት መጀመሪያ ከአንድ ወር ተኩል በኋላ ይሆናል፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG