No media source currently available
የከተራ በዓል ትላንት ሲከበርና ዛሬም ታቦታት ከማደሪያቸው ወደ የደብራቸው ሲመለሱ ችግር አጋጥሟቸው እንደነበረ የሐረር ከተማ ምዕመናንና የሃይማኖት አባቶች አስታውቀዋል። በጥቃቱ በሁለቱም ቀናት የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውንና ንብረት መውደሙንም ቪኦኤ ያነጋገራቸው እማኞች ገልፀዋል። የግጭቱ መንስዔ "በመስጂድና የቅዱስ ቁርዓን ሃውልት ላይ ጥቃት ደርሷል" ተብሎ በመወራቱ ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ “ልሙጡን ባንዲራ በመቃወም ነው” የሚሉም አሉ።