የድርጅቱ ምክትል ዲሬክተር አቶ መብርሂ ብርሃነ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሲናገሩ፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የወጣው ደንብ፥ በጦርነቱ ወቅት ለወጡትና ከሕገ መንግሥቱ ጋራ ለሚቃረኑት ሕጎች እውቅና የሚሰጥ መኾኑን ገልጸዋል፡፡
ድርጅታቸው፣ ዐዲሱ ደንብ እንዲሻር፣ ለፌደራል የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አቤቱታ ማቅረቡን አመልክተዋል፡፡ጉባኤውም አቤቱታውን በመመልከት፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥበት ማዘዙን ተናግረዋል፡፡
ፍትሕ ሚኒስቴርም በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ታዟል። ስለ ጉዳዩ ከትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ፡፡