No media source currently available
ከትግራይ ክልል የተመደቡ አዲስ ተማሪዎችን ለጉዳት የሚዳርግ ምንም ዓይነት የደኅንነት ሥጋት በአማራ ክልል ውስጥ እንደሌለና ተማሪዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናቸውን የወሎና የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲዎች አስታወቁ፡፡ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከትግራይ ክልል የተመደቡ ተማሪዎችን እየተቀበሉ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡