በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ የችሎት ውሎ


ፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሣለኝ
ፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሣለኝ




please wait

No media source currently available

0:00 0:02:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ቀደም ሲል ግንቦት 22/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ የመከላከያ ምሥክሮቹን ዛሬ - ማክሰኞ ሐምሌ 2/2005 ዓ.ም ማሰማት ጀምሯል፡፡

ዶ/ር ያሬድ ለገሠ እና ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ለምሥክርነት ቀርበዋል፡፡

“የመንግሥትን ስም ማጥፋት” የሚለው ድንጋጌ ሃሣብን ከመግለፅ መብትና ከሃገሪቱ ሕገመንግሥትም ጋር የሚቃረን መሆኑን የሕግ ምሁሩ ዶ/ር ያሬድ ለገሠ ለፍርድ ቤት ገልፀዋል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ‘የመንግሥት ድርጊቶች ናቸው’ ብሎ የዘረዘራቸው በሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ - ሰመጉ ሪፖርቶች የተረጋገጡ መሆናቸውንም የድርጅቱ መሥራችና የቀድሞ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡

ሦስተኛውን የመከላከያ ምሥክር ለመስማት በዕለቱ ጊዜ የሌለው መሆኑን ፍርድ ቤቱ ካስረዳ በኋላ ለሐምሌ 23/2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ዝርዝሩን መለስካቸው አምሃ ከአዲስ አበባ ያጠናቀረውን ዘገባ ከያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG