በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታንዛኒያ የንግድ መዲና ዳሬሰላም ውሃ አጥሯታል


የታንዛኒያ የንግድ መዲና ዳሬሰላም ውሃ አጥሯታል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:40 0:00

የታንዛኒያ የንግድ ዋና ከተማ የሆነችው ዳሬሰላም ዋነኛው የውሃ ምንጭ የሆነው ሩቩ ወንዝ እየቀነሰ በመምጣቱ ነዋሪዎችዋን በውሃ የራሽን ኮታ ውስጥ ካስገባች አንድ ወር ሆነ፡፡

ባለሥልጣናቱ የውሃው አቅርቦት ችግር ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ቢገልጹም ተችዎች ግን የሃብት አጠቃቀም አስተዳደር ጉድለት በመኖሩ ነው ይላሉ፡፡ የ39 ዓመቷ የዳሬ ሰላም ነዋሪ ሀሊማ ኦትማን ለእለት ፍጆታዋ ውሃ የምትገዛው ከግል የውሃ ጉድጓድ ነው፡፡

እንደ ኦትማን ያሉ ነዋሪዎች በከተማው ባለ የውሃ እጥረት የተነሳ ከአንድ ወር በላይ ለሚሆን ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን ውሃ ከነጋዴዎች መግዛት ተገደዋል፡፡

“ከዚህ በፊት አንድ ጋሎን በአምስት መቶ ሽልንግ እንገዛ ነበር፡፡ አሁን ግን ከአንድ ሺ አምስት መቶ እስከ ሁለት ሺ ገብቷል፡፡” የምትለው ኦትማን “ዝቀተኛ ገቢ ላለን ለኛ ለዜጎቹ ያ ብዙ ገንዘብ ነው፡፡ ቤተሰብ አለኝ ስለዚህ ስንት ጋሎን ውሃ ነው መግዛት ያለብኝ? የሚያስወጣን ወጭ ብዙ በመሆኑ አንችለውም” ብላለች፡፡

በጥቅምት ወር መጨረሻ የዳሬሰላም ባለሥልጣናት የውሃ እጠረት መፈጠሩን አስታውቀው 5 ሚሊዮን ነዋሪዎች ባሏት የታንዛኒያ ትልቋ ከተማ ውስጥ ውሃን በራሽን ኮታ ማደል ጀምረዋል፡፡

ባለሥልጣናቱ በተፈጠረው ድርቅ ሁኔታ የከተማው ትልቁ የውሃ ምንጭ ከሆነው ሩቩ ወንዝ የሚገኘው ውሃ በቀን ወደ 300 ሚሊዮን ሊትር ወርዷል ይላሉ፡፡ ከተማው የሚፈልገው የውሃ መጠን ግን 450 ሚሊዮን ሊትር መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ተችዎች የታንዛኒያ ባለሥልጣናት ለድርቁ በሚገባ መዘጋጀት ነበረባቸው ይላሉ፡፡

“ይህን የምናሳብበው በዝናብ መጥፋት ነው፡፡ ለረጅም ጊዜ ዝናብ የማያገኙት እነዚያ አገሮች ታዲያ እንዴት ቻሉት?” የሚሉት የቀድሞ የኡቡንጎ አውራጃ ከንቲባ ቦኒ ፌስ ጃኮብ “እንደ አረብ ኤምሬት ወይም በሰሃራ በረሃ ያሉ አገሮችን ይጠቅሳሉ፡፡”

“መንግሥት ለውሃው ዘርፍ ቅድሚያ አለመስጠቱም ይታያል፡፡” ብለዋል ጃኮብ፡፡

የውሃ እጥረቱ በጊዜ የማይፈታ ከሆነ የታንዛኒያን ኢኮኖሚ ሊጎዳ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

የአገሪቱ ብሄራዊ ስታትስቲክስ ጽ/ቤት ዳሬሰላም 80 ከመቶ የሚሆኑ የታንዛኒያ የኢንደስትሪ እንቅስቃሴዎች የሚገኙባት ከተማ መሆንዋን ይገልጻል፡፡

የአየር ትንበያ ባለሙያዎች የውሃ እጥረቱ የሚያበቃበት ጊዜ ተቃርቧል ይላሉ፡፡

በታንዛኒያ ሜትሮሎጂ የአየር ትንበያ ባለሙያ የሆኑት ጆሲ ማዋታ

“አሁን ወደ ታህሳስ እየገባን ስለሆነ ዝናቡ ይጨምራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ዝናብ የተለያዩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ይረዳል፡፡ ሰዎች ለቤት ውስጥ ፍጆታቸው የዝናብን ውሃ ስለሚጠቀሙ የውሃ እጥረቱ ይቀንሳል፡፡” ብለዋል፡፡

እስከዚያው ድረስ ባለቻት ውሃ እየተገለገለች ያለችው ኦትማን ዝናብና ዘላቂ የውሃ አቅርቦት ይመለሳል ብላ ተስፋ ማድረጓን ቀጥላለች፡፡

XS
SM
MD
LG