በአገሪቱ፣ በጠለፋ እና የአስገድዶ መድፈር ፈጻሚ ወንጀለኞች ላይ ተመጣጣኝ የሕግ ቅጣቶች እየተሰጡ አለመኾናቸውን የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ለመሰል ወንጀሎች እና ጎጂ ድርጊቶች መስፋፋት አንዱ ገፊ ምክንያት እየኾነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ/ኢዜማ/ ፓርቲም፣ ጠለፋ እና አስገድዶ መድፈር ተደራራቢ ወንጀሎች መኾናቸውን ገልጾ፣ የሚተላለፉ የቅጣት ውሳኔዎች ግን አስተማሪ እና ተመጣጣኝ አይደሉም፤ ብሏል፡፡
በአንጻሩ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን የጎርካ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ ሰሞኑን ባዋለው ችሎት፣ በአዳጊ ሴት ተማሪዎች ጠለፋና የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩ 12 ግለሰቦች ውስጥ፣ ዘጠኝ ተከሳሾች፣ ከአንድ ዓመት እስከ 19 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡