በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋሞ እና በጎፋ ዞኖች በተዛመተው ኮሌራ ሰዎች እየሞቱና በብዛት እየታመሙ ናቸው


በጋሞ እና በጎፋ ዞኖች በተዛመተው ኮሌራ ሰዎች እየሞቱና በብዛት እየታመሙ ናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:54 0:00

በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን በተከሠተው የኮሌራ ወረርሽኝ፣ ስምንት ሰዎች መሞታቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ ሲያስታውቅ፣ በጋሞ እና በጎፋ ዞኖች፣ እስከ ትላንት ድረስ በጥቅሉ ከ430 በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን፣ የየዞኖቹ ባለሥልጣናትና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች፣ ድጋፍ እያደረጉ ቢኾንም፣ የመድኃኒት እና የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት መኖሩን አመልክተዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት(OCHA)፣ ሰሞኑን በአወጣው ሪፖርት፣ እ.አ.አ. ካለፈው ዓመት ነሐሴ ወር አንሥቶ፣ የደቡብ ክልልን ጨምሮ በሌሎች ክልሎችም በተከሠተው ወረርሽኝ፣ ከአራት ሺሕ በላይ ሰዎች መያዛቸውንና 71 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG