በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሸበሌ ወንዝ ሙላት በሁለት የሶማሌ ክልል ወረዳዎች ሰብሎችን ማውደሙ ተገለጸ


 የሸበሌ ወንዝ ሙላት በሁለት የሶማሌ ክልል ወረዳዎች ሰብሎችን ማውደሙ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:27 0:00

በባሌ ተራራማ ስፍራዎች የጣለውን ከባድ ዝናም ተከትሎ ከወሰኑ አልፎ የሞላው የሸበሌ ወንዝ ባስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በሶማሌ ክልል ሁለት ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ የእርሻ ማሳዎችን ማውደሙ ተገለጸ፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት፣ ነዋሪዎችን ከወንዙ ዳርቻ በማንሣት በከፍተኛ ቦታዎች የማስፈር ሥራ መሠራቱን ያስታወሰው የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ፣ ጎርፉ፥ በሰው፣ በእንስሳት እና በመሠረተ ልማት ላይ ያደረሰው ጉዳት አለመኖሩን አስታውቋል።

በያዝነው ነሐሴ ወር፣ ከባድ ዝናብ ሊጥል እንደሚችል በትንበያው ያመለከተው የብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በወንዙ ተፋሰስ ዙሪያ ያሉ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

XS
SM
MD
LG