በሶማሌ ክልል፣ ለሳምንታት በጣለው ዝናም፣ የተጎዱ እና የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር፣ ባለፈው ሳምንት ብቻ ከዕጥፍ በላይ እንደጨመረ ክልሉ አስታወቀ።
ክልሉ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጸው፣ ከፌዴራል መንግሥት ጋራ በመተባበር ለተጎጂዎች ድጋፍ እያደረሰ ሲኾን፣ የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎችን በዘላቂነት ከስጋት ነጻ ለማድረግም ታስቧል፡፡
የጎርፉ መንሥኤ ኤልኒኖ እንደኾነ የገለጸው የብሔራዊ ሜቲዮሮሎጂ ባለሥልጣን፣ በተከታዩ ሳምንትም እንደሚቀጥልና ከዚያ በኋላ ባሉት ሳምንታት ግን፣ ዝናሙ ባይቆምም የጎርፉ መጠን እየቀነሰ እንደሚሔድ ጠቁሟል።