በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ተመተትው የወደቁት ነገሮች የቻይናዎቹን ፊኛዎች ይመስላሉ” - ሻክ ሹመር


“ተመተትው የወደቁት ነገሮች የቻይናዎቹን ፊኛዎች ይመስላሉ” - ሻክ ሹመር
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:41 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ ተዋጊ ጀቶች በዩናይትድ ስቴትስ እና ካናዳ የግዛት ክልል ላይ ሲበሩ የነበሩ ሁለት ግኡዝ ነገሮችን መትተው ጥለዋል፡፡ ምንም እንኳ ተመተው ስለ ወደቁት ስብስርባሪዎቹ የተሟሉ ተጨማሪ ትንተናዎች የሚያስፈልጉ ቢሆንም በህግ መወሰኛው ከፍተኛው የዴሞክራት አባልና መሪ ሻክ ሹመር የተባለው ነገር ከቻይናው ፊኛ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

የሁለቱ አገር መሪዎች ይሁንታ ከሰጡ በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ኤፍ 22 ተዋጊ ጀቶች በሰሜን አሜሪካ ላይ የነበሩትን ሁለት ጉእዝ ነገሮችን መተው ጥለዋል፡፡ በብሄራዊ የጸጥታ አማካሪው ማብራሪያ ከተሰጣቸው በኋላ ዴሞክራቱ ቻክ ሹመር ለኤቢሲ ቴሌቪዥን “በዚህ ሳምንት” አሁን ፊኛዎች መሆናቸውን እንዳመኑ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ በቀደመው ሳምንት ተመቶ እንደወደቀው እንደ ቻይና ፊኛ ትልቅ አለመሆናቸውን ሹመር ሲገልጹ “ከዚህ ቀደም ከነበረው እጅግ ያነሱ ናቸው፡፡ አንደኛው በካናዳ አንደኛው አላስካ ላይ 40ሺ ጫማዎች ከፍታ ላይ ነበሩ ፡፡ ያ ለንግድ አውሮፕላኖች እጅግ አደገኛ መሆኑ የተወሰነው ወዲያኑ ነበር፡፡” ብለዋል፡፡

እነዚህ ሦስት ነገሮች ስለነበራቸው አቅምና ምንነት፣ ተመተው ከወደቁ ስብርባሪዎቹ የተሟላ መረጃ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ እስካሁን ያልተመለሱ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡

ዴሞክራቱ የህዝብ እንደራሴ ጂም ሂመስ ከኤንቢሲ ቴሌቭዝን ጋር በነበራቸው ቆይታ “አስተዳደሩ ስለሚያውቃቸው ነገሮች ያለውን መረጃ ሁሉ ወደፊት ቀርቦ ማስረዳት ባለመቻሉ እውነተኛ ቅሬታ አለኝ፡፡” ብለዋል፡፡“ ይሁን እንጂ እዚህ ላይ የችግሩ አንዱ ክፍል ሁለተኛው እና ሶስተኛው ግኡዝ ነገሮች እጅግ ሩቅ በሆነ አካባቢ ተመተው ወድቀዋል፡፡ ስለዚህ ግምቴ ማካፈል የሚቻል ብዙ መረጃ ገና የሌለ መሆኑን ነው፡፡” ሲሉም እንደራሴው አያይዘው ተናግረዋል፡፡

የሪፐብሊካን የህዝብ እንደራሴ ማይክ ተርነር ለሲ ኤን ኤን “ሁኔታውን ከግምት በማስገባት የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሥርዓትን የበለጠ ማጠናከር ያስፈልጋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“የተሟላ የራዳር ሥርዓት የለንም በርግጥም የተቀናጀ የሚሳዬል ሥርዓት የለንም፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ክልል እንዴት አድርገን መከላከል እንደምንችል ልናስብ ይገባናል፡፡” ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ሪብሊካኑ እንደራሴ ጄምስ ካመር ለኤቢሲ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ደግሞ የባይደን አስተዳደር ጉዳዩን አጥብቆ በመመልከቱ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

“ይሁን እንጂ ከቻይና ጋር ሊፈቱ የሚገቡ ትልቅ ችግሮች አሉ” ካሉ በኋላ ቻይናውያን “የዓለምን ኢኮኖሚ ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ሙከራ ልክ የመንገድና የመቀነት ተነሳሽነት (ቤልት ኤንድ ሮድ) እያደገ እነደመጣው ሁሉ፣ የጦር ኃይላቸውም እያደገና እያሰፋ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ካመር ቻይና በበርካታ አገሮች ስላሏት የመሰረት ልማት ፕሮጀክቶች ኢንቨስትመንት ነበር የተናገሩት፡፡

የፔንታገን ባለሥልጣናት በአላስካ አየር ላይ የተመታው ግኡዝ ነገር ወደ በረዶነት በተቀየረ ውሃ ላይ መውደቁን ተናግረዋል፡፡

በአትላንቲክ ውሃ ላይ ከወደቀው ትልቅ ፊኛ ይህኛው ምንነቱን ለማወቅ በቶሎ ይደረስበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የካናዳ ኃይሎች በዩኮን ግዛት መትተው የጣሉትን ግኡዝ ነገር ስብርባሪ ያገኙት ወዲያው ነበር፡፡

XS
SM
MD
LG