ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
በቦስተን ማራቶን ላይ ከተፈፀመው የፈንጂ ጥቃት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር የቆየውና ክሥ የተመሠረተበት ወላጆቹ ትውልድ ኢትዮጵያ የሆኑት ሮቤል ፊሊጶስ የተከሰሰበት ጉዳይ ቀደም ሲል ይነገር የነበረውን ያህል እንዳልሆነና ወደፊት በሚካሄደው የፍርድ ሂደትም አወታዊ ውጤት እንደሚጠብቁ ጠበቃው ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ አስታወቁ፡፡
አቶ ደረጀ ደምሴ - የሮቤል ፊሊጶስ ጠበቃ
ቦስተን ማሣቹሴትስ የሚገኙት የሮቤል ፊሊጶስ ጠበቃ አቶ ደረጀ ደምሴ ሲናገሩ ሮቤል በፃርናየቭ ወንድማማቾች ከተፈፀመው አድራጎት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ብለዋል፡፡
ሮቤል ፊሊጶስ - የሰዓሊ ንድፍ
ሮቤል ፊሊጶስ በመቶ ሺህ ዶላር ዋስትና እንዲለቀቅ ጉዳዩን የያዘው ፌደራል ፍርድ ቤት ትናንት የወሰነ ሲሆን ጉዳዩ በሚታይበት ጊዜም ከቤተሰቦቹ ጋር በቤት ውስጥ እሥር እንዲቆይ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡
ሮቤል ፊሊጶስ
ጉዳዩ ፌደራል በመሆኑ የፍርዱ ሂደት ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ሊዘልቅ እንደሚችል ጠበቃው አቶ ደረጀ ደምሴ ጠቁመው ለፊታችን ግንቦት ዘጠኝ መቀጠሩን ገልፀዋል፡፡
ተጨማሪና ዝርዝር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ፡፡
Embed
share
Embed
share
The code has been copied to your clipboard.
The URL has been copied to your clipboard
No media source currently available
ቀጥተኛ መገናኛ