በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች በቆቦ


የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች በቆቦ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:51 0:00

ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በሰሜን ወሎዋ ቆቦ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ የተጠለሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች በምግብና በመሰረታዊ ድጋፍ አቅርቦት መቸገራቸውን ገለጹ። በመቶዎች የሚቆጠሩት ተፈናቃዮች በትግራይ ክልል ባለው የምግብና የፀጥታ ችግር ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ተፈናቅለው ወደ ቆቦ መግባት ከጀመሩ ሁለት ሳምንት እንደሆናቸው ተነግሯል።

የራያ ቆቦ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው የመጡት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ መደበኛ የወንጀል መከላከልና ጸጥታ የማስከብር ሥራው ላይ ተፅዕኖ እንዳሳረፈበት ገልጿል። ጽ/ቤቱ የክልሉና የፌዴራል መንግሥቱ ተፈናቃዮቹን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያንቀሳቅስ ጠይቋል።

የትግራይ ክልል የውጭ ግንኙነት አስተባባሪ መሆናቸውን የሚናገሩት ካናዳ የሚገኙት አቶ ዮሃንስ አብርሃም ነዋሪዎች ከቀናት በፊት ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት የስልክ ምለሽ ከቤተሰብ ጋር ለመገናኘት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውጭ ምግብ ፍለጋ እንደስደተኝነት ሊመደብ የሚችል የሚታወቅ እንቅስቃሴ እንደሌለ ገልፀው ነበር።

XS
SM
MD
LG