ዋሺንግተን ዲ.ሲ፣ ጆሃንስበርግ፣ አዳስ አበባ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እያደረጉ ባሉት ጉብኝታቸው በሶዌቶ ስፋት ያለው ታዳሚ በተገኘበት የስብሰባ አዳራሽ ንግግር አድርገዋል፤ ከተሰብሳቢው ጋርም ተወያይተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በዚሁ የሶዌቶ ንግግራቸው የኔልሰን ማንዴላንና የዴዝሞንድ ቱቱን ገድል አስታውሰው “ለማዲባ ከሚፀልየው የዓለም ማኅበረሰብ ጋር ነን” ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ የዛሬ ሦስት ዓመት አካባቢ ባስጀመሩት መርኃግብር አማካይነት የአፍሪካ ወጣቶች በአዳዲስ ክኅሎቶች፣ በሥራ ፈጠራ፣ በአመራር፣ ትምህርት፣ ጤናና ቴክኖሎጂን በመሣሰሉ ዘርፎች በአዲስ የትብብር አጋርነት ስሜት እንዲታነፁና የውሣኔ ሰጭነት አቅማቸው እንዲጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
የፕሬዚዳንት ኦባማን ጉብኝት የተቃወሙ ሰልፈኞች ደግሞ አሜሪካ በአፍሪካ የምታካሂደውን የድሮኖች ጥቃት አውግዘዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በጉብኝታቸው መርኃግብር ውስጥ ኢትዮጵያንም ማካተት ነበረባቸው ሲሉ ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የተለየ አስተያየት ያንፀባረቁም አሉ።
“ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በአፍሪካ የሚያደጉት ጉብኝት ሁለት መልክ የያዘ ነው” ብለዋል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ።
ለመሆኑ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝት በሦስቱ ሃገሮች /በሴኔጋል፣ በደቡብ አፍሪካና በታንዛኒያ/ እንዲሆን ለምንና እንዴት ተወሰነ? ዲፕሎማትና የውጭ ግንኙነቶች መምህር ዴቪድ ሺን ትንታኔ ይሰጡናል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች አፍሪካን መርገጥ ከጀመሩ ሰባ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
የመጀመሪያው ፍራንክሊን ሩዘቬልት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ምክንያት ከተባበሩት ኃይሎች አጋሮቻቸው ለመመካከር ነበር ካሣብላንካና ካይሮ የተገኙት፤ ከእርሣቸው በኋላ ጂሚ ካርተር፣ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን፣ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ከፕሬዚዳንትነታቸው ዘመናት በኋላም በአፍሪካ የተለያዩ ሰብዓዊ ተግባራትን እያከናወኑ ነው፡፡
ለዝርዝር ዘገባዎች የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡