በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለማችን የግዙፉና ጠንካራው ዴሞክራሲ በዓል ተከበረ


እጅግ የተካረረውና ተጧጡፎ የሰነበተው እንዲሁም ረዘም ላለ ጊዜ የተካሄደው የአሜሪካ አጠቃላይ ምርጫ ትናንት ተካሂዷል፤ የአሜሪካ ሕዝብ ለነባሩ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአብላጫ ድምፁና በምርጫ ውክልናም በተጨማሪ አራት ዓመታት የሁለተኛ ዘመን የዋይት ኃውስ ዕድሜ ቸሯቸዋል፡፡



please wait

No media source currently available

0:00 0:25:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ለዩናይትድ ስቴትስ ዴሞክራቲክ ፓርቲ የትናንትናው ምሽት በእጅጉ የደመቀና የከበረ ነበር፡፡
የፓርቲው ብሔራዊ ኮሚቴ ዋና ፅ/ቤት ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ላይ በካፒቶል ሂል ላይዘን ሆቴል አዘጋጅቶት በነበረው የምርጫ ውጤት መከታተያ ፕሮግራሙ ላይ የፓርቲው መሪዎች፣ ደጋፊዎችና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰጭዎች ተገኝተው የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን መመረጥ እጅግ በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል፡፡


የሪፐብሊካን ፓርቲው ብሔራዊ ኮሚቴ ያዘጋጀው ፕሮግራም መጀመሪያው ላይ በእጅጉ የተነሣሣ፣ በማሸነፍ ተስፋና ስሜት የተሞላ የነበረ ቢሆንም ወደ ኋላ ግን በፀጥታ ተውጧል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የዩናይትድ ስቴትሷ ዋና ከተማ የዋሽንግተን ዲሲ ብዙዎቹ ጎዳናዎችና የዋይት ኃውስ ቤተመንግሥት አካባቢ በድል ጭፈራና በሆታ የተሞሉና የደመቁ ሆነው ሌሊቱን አሣልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዳግም እንዲመረጡ ድምፃችንን መስጠት ብቻ ሳይሆን በተለያየ መልክ ያቅማችንን አስተዋጽዖም አበርክተናል ያሉ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ውጤቱንም ባንድነት ለመስማት አርሊንግተን ቨርጂንያ በሚገኘው ዳማ ምግብ ቤት ተሰባስበው አምሽተዋል።
የዳማ ምግብ ቤት ሠራተኞችና ደንበኞቻቸው ከአራት ዓመት በፊትም ኦባማን ለማስመረጥና ውጤቱን በጋራ ለመከታተል ተመሣሣይ ፕሮግራም አዘጋጅተው እንደነበር ይታወሣል፡፡

ሰሎሞን አባተ የዴሞክራቲክ ፓርቲውን ብሔራዊ ኮሚቴ፣ ሄኖክ ሰማእግዜር የሪፐብሊካን ፓርቲውን ዝግጅቶች እና የከተማይቱን ድኅረ ምርጫ ፈንጠዝያ፣ እንዲሁም ሰሎሞን ክፍሌ የዳማ ሬስቶራንትን ሥነ-ሥርዓት ተከታትለዋል፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG