በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዝዳንት ኦባማ 2ተኛ ዙር የአስተዳደር ዘመንና አገሪቱ የገጠሟት ፈተናዎች፤


U.S. President Barack Obama gives his election night victory speech in Chicago, November 7, 2012.
U.S. President Barack Obama gives his election night victory speech in Chicago, November 7, 2012.
የፕሬዝዳንት ኦባማ 2ተኛ ዙር የአስተዳደር ዘመን ገጽታ፤
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኦባማ ለሁለተኛ ዙር አገራቸውን በፕሬዝዳንትነት ለማስተዳደር ያስቻላቸውን ምርጫ ባሸነፉ ማግስት ከፊታቸው የተደቀኑ ፈተናዎች ለመፍታት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች መመርመር ይዘዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አብላጫ መቀመጫዎችን ከያዘው ከተፎካካሪው የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ጋር አብሮ ለመሥራት ሁለቱ ወገኖች በየፊናቸው ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል። መሠረታዊ የፍልስፍናና የአመለካት ልዩነቶቻቸው ለሚንጸባረቁባቸው ለእነኚህ ቁልፍ-ቁልፍ ችግሮች እልባት ለማበጀት ግን “እንዴት?” የሚለው አሁንም ያልተመለሰ ጥያቄ ነው።
ለመሆኑ ቀጣዩ የሁለተኛ ዙር የአስተዳደር ዘመናቸው ምን ዓይነት ገጽታ ይኖረው ይሆን? የትንታኔ ውይይታችን ያተኩርበታል።

ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን፥ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም በካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የካሊፎኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የኅግ ባለ ሞያ እንዲሁም ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ በሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ናቸው።
XS
SM
MD
LG