No media source currently available
ምዕራብ ኦሮምያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ሸማቂዎች ላይ መንግሥት ዕርምጃ እየወሰደ መሆኑን የኦሮምያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃልፊ አቶ ታዬ ደንደአ ለቪኦኤ ገልፀዋል። “ከሸማቂዎቹ ጋር የሚደረግ ድርድር የለም” ብለዋል የፓርቲው ቃል አቀባይ። የሸማቂዎቹ የምሥራቅና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ መሪ “በእርምጃው እየተጎዳ ያለው ህዝቡ ነው” ብለዋል።