No media source currently available
በኦሮምያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በትናንትናው ዕለት አልፎ አልፎ የትራንስፖርት ፍሰት እክል በማጋጠሙ መቸገራቸውን ቮኦኤ ያነጋገራቸው ነጋዴዎች እና አሽከርካሪዎች ገለፁ። ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎችም መኖራቸውን ተናግረዋል። የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ የኢትዮጵያን ሰላም ለማወኩ የተደረጉ ሙከራዎች ከሽፈዋል ብሏል።