በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦክላሆማው አውሎ ነፋስ ተጎጂዎችን መፈለጉ ቀጥሏል፤ የአየር ሁኔታው አሁንም ከባድ ነው

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:52 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


በአውሎ ነፋሱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እስከአሁን [መጨረሻ ላይ በደረሱን መረጃዎች መሠረት] 24 መድረሱና 240 ሰው መቁሰሉ ተገልጿል፡፡ የሟቾች ቁጥር ከሃምሣ መብለጡን የሚጠቁሙ ዘገባዎች ቀደም ሲል ተሰምተዋል፡፡

በሰዓት የ320 ኪሎሜትሮች ፍጥነት ያስመዘገበው ኃይለኛው አውሎ ነፋስ ሞር የተባለ የኦክላሆማ ሲቲ የሕዝብ መኖሪያ ሠፈሮችን ሰፊ ክፍል በአጠቃላይ አውድሟል።

​የቤቶች ፍርስራሽና የሌሎች እንደ ተሽከርካሪ ያሉ ስብርባሪዎችና በራሪዎች በኃይለኛው ንፋስ ወደ ሰማይ እየተበተኑ ተጨማሪ የአካል ጉዳት ማደረሳቸው ታውቋል።

ሦስት ኪሎ ሜትሮች ስፋት ያለው ኃይለኛ ነፋስ የቀላቀለ ዶፍ ያለፈባቸው ሁለት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ልጆች ትምህርት ላይ እንዳሉ ወድመዋል፡፡ በሕንፃዎቹ ፍርስራሽ ሥር ብዙ ልጆች ተቀብረዋል ተብሏል፡፡

የአስቸኳይ እርዳታ ሠራተኞች ፍርስራሹን ቆፍረው ብዙ ልጆችን አትርፈዋል፡፡ ሆኖም ትላንት ከመሸ በኋላ ሌሎችን በሕይወት የማግኘት ተስፋ እየተመናመነ መሄዱ ሲነገር ተሰምቷል፡፡

ይሁን እንጂ የቆሰሉና የጠፉ ሰዎችን ፍለጋ አሁንም ቀጥሏል።

ፕሬዚደንት አባማ ማምሻውን ባደረጉት ንግግር በኦክላሆማ የተፈጥሮ ቀውስ መከሰቱን በማወጅ አስፈላጊው የአጣዳፊ ጊዜ እርዳታ ሁሉ ለግዛቲቱ እንዲሰጥ የፌዴራል የአስቸኳይ እርዳታ አስተዳደር መሥሪያ ቤትን አዝዘዋል።

በብሔራዊ የአየር ሁኔታ ክትትልና ትንበያ ድርጅት መረጃ መሠረት ኦክላሆማን የመታው አውሎ ነፋስ እስከ ዛሬ በአካባቢው ከተከሰተው “ሁለተኛውና እጅግ ሃይለኛው ነው” ተብሏል።

ለተጨማሪ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG