ተቃዋሚው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፣ በዐማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በቀጠሉ ግጭቶች ውስጥ የሚሳተፉ አካላት፣ የግጭት ምክንያቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ውይይት እንዲጀምሩ አሳስቧል።
ፓርቲው፣ ዐዲስ አበባ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤቱ ትላንት እሑድ በሰጠው መግለጫ፣ ለግጭቶቹ አልባት ለማስገኘት መንግሥት የመሪነቱን ሚና መውሰድ እንዳለበት፣ ሊቀ መንበሩ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ኀይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ “መንግሥት እንደ ሀገር ሰላም ለማስፈን እየሠራ ነው፤” ብለዋል፡፡