በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ “የመመለሻ በር” ዐውደ ትርኢት የአፍሪካ ዲያስፖራዎችን ለማስተሳሰር አልሟል


please wait
  • Auto
  • 240p
  • 360p
  • 480p
  • 720p

No media source currently available

0:00 3:51 0:00
  • Auto
  • 240p
  • 360p
  • 480p
  • 720p

የናይጄሪያ የንግድ ከተማ የኾነችው ሌጎስ፣ “የመመለሻ በር” የተሰኘውን ዐውደ ትርኢት አራተኛ ዙር፣ ባለፈው ሳምንት አስተናግዳለች።

ዓመታዊው ዐውደ ትርኢት፣ የአፍሪካ ተወላጅነት ያላቸው ዲያስፖራዎች፣ ቅድመ አያቶቻቸው ለባርነት ከአፍሪካ ተጭነው በወጡበት መንገድ ወደ ጥንተ ርስታቸው የሚመለሱበት ልዩ ዝግጅት ነው።

ከጥቅምት 8 እስከ 21 ቀን ድረስ ለተካሔደውና ለ13 ቀናት ለዘለቀው ክብረ በዓል፣ አንዳንድ የአፍሪካ ዲያስፖራዎች፣ በጀልባ ተጉዘው ወደብ ላይ ደርሰዋል፡፡ ይኸው ጉዞ፣ ከ400 ዓመታት በፊት፣ ከተመሳሳይ ወደብ በባርነት የተወሰዱ በሺሕዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያንን፣ ወደ ምድረ ርስታቸው መመለስን እንደሚያመላክት ተገልጿል።

አፍሪካውያን ባሪያዎች፣ በሰንሰለት ታስረው ወደሚጫኑበት የንግድ መርከብ ያደርጉት የነበረውን አሰልቺ የእግር ጉዞ ለማዘከርም፣ ወደ ውቅያኖሱ የሚወስደውን የ1ነጥብ5 ኪሎ ሜትር መንገድ ተጉዘዋል።

ከጃማይካዊ ወላጆቹ ተገኝቶ በዲያስፖራ የሚኖረው የፓን አፍሪካ አቀንቃኝ ማርከስ ጋርቬይ፣ በዝግጅቱ የተሰማውን ሲገልጽ፥ “ከባድ እና አድካሚ ተሞክሮ ነበር። ዕድለኛ ኾነን፣ እኛ እንደ ቅድመ አያቶቻችን በሰንሰለት ባንታሰርም፣ ውስጣችንን ግን እየተሰማን ነበር፤” ብሏል።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን፣ በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ወደቦች በኩል፣ ወደ አሜሪካ እና የካሪቢያን ሀገራት ተወስደው ለባርነት ተዳርገዋል፤ የቅኝ ገዥዎችንም ይዞታዎች አገልግለዋል።

አንዳንዴ በዘመዶቻቸው ወይም በተቀናቃኝ ጎሣዎች አልያም በእርስ በርስ ጦርነቶች ወቅት ተይዘው ለባርነት የተሸጡ አፍሪካውያን፣ ሩቁን የባሕር ጉዞ ከመጋፈጣቸው በፊት፣ በባሕሩ ዳርቻ ላይ የእግር ጉዞ ያደርጋሉ። ብዙዎቹ በእነዚያ ጉዞዎች

ወቅት ለሞት ቢዳረጉም፣ በሕይወት መድረስ የቻሉት፥ በስኳር፣ በትምባሆ እና በጥጥ እርሻዎች ውስጥ የነበረባቸውን ከፍተኛ የሥራ ጫና ተቋቁመው ለማለፍ ችለዋል።

በክብረ በዓሉ ላይ የታደሙት እንግዶች፣ ባሮች፥ ቁጡ እና ተፋላሚ እንዳይኾኑ ያደርጋቸዋል፤ በሚል እንዲጠጡ የሚገደዱትን የጉድጓድ ውኃ ጨምሮ፣ ሌሎች ከምእተ ዓመታት በፊት የነበሩ ታሪካዊ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል። “ሦስት የተለያዩ ዝርያዎች አሉብን፤” የምትለው አፍሪካዊ ዝርያ ያላት ስፔናዊዋ ራጋሬ ሮሜሮ፣ “ከነዚኽ ውስጥ የአፍሪካ ዝርያዎቻችን ያለፉበትን መረዳት እፈልጋለኹ። ይህ ለእኔ በጣም ጠቃሚ ነገር ነው። ለዓመታት በተሳሳቱ መረጃዎች ውስጥ ላለፉ ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼም፣ ጥሩ እና ትክክለኛ መረጃ እወስድላቸዋለኹ፤” ትላለች።

ከረጅም የእግር ጉዞ በኋላ፣ እንግዶቹ፥ በ“መመለሻው በር” በኩል የሚጠጣ እንደሚቀርብላቸው፣ የናይጄሪያ ዲያስፖራ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቢኬ ዳቢሪ ያስረዳሉ።

ይህም “ኢኮኖሚያዊ፣ መንፈሳዊ፣ ስሜታዊ እና አካላዊ የኾነ ተምሳሌታዊ ግንኙነት” እንደኾነ የሚያስረዱት ዳቢሪ፣ “ከአንድ ሰው ጋራ የበለጠ ስታወራ የሰውዬውን ማንነት በደንብ ትረዳዋለኽ፤ አሃ፤ ማንነትኽ ይኼ ነው? እንደገመትኹት መጥፎ ሰው አይደለኽም፤” ትላለኽ። ወደዚኽ ሲመጡ ደግሞ ለአህጉሩ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ማየት ይፈልጋሉ። ለምሳሌ፡- እዚኽ ባዳግሪ ውስጥ፣ የዲያስፖራ ቦታ መገንባት ሊኾን ይችላል። ለአህጉሩም መዋዕለ ነዋይ ማፍሰሻ መንገድ ነው።”

በሌጎስ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ባዳግሪ፣ በአትላንቲክ የባሪያ ንግድ ወቅት፣ ከፍተኛ የባሪያ ወደብ ኾኖ ያገለገለ ስፍራ ነው። ግምቶች በሰፊው ቢለያዩም፣ እ.አ.አ ከ15ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ባለው ጊዜ ውስጥ፣ ከ10 እስከ 28 ሚሊዮን አፍሪካውያን፣ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ተጭነው ተወስደዋል፤ ተብሎ ይታመናል።

XS
SM
MD
LG