በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ ቤተክርስቲያናት ከጥቃቱ በኋላ ጥበቃቸውን አጠናክረዋል


የናይጄሪያ ቤተክርስቲያናት ከጥቃቱ በኋላ ጥበቃቸውን አጠናክረዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:33 0:00

በናይጄሪያ ምዕራባዊ የአገሪቱ ክፍል የሚገኙት የእስላማዊ መንግሥት ታጣቂዎች እ.ኤ.አ ሰኔ 5፣ በካቶሊክ ቤተክርስቲያናት ላይ ባደረሱት ጥቃት ሰዎች ከተገደሉ ወዲህ፣ የናይጄሪያ ቤተክርስቲያናት ታጣቂ ጠባቂዎችና የመግቢያ ላይ ፍትሻዎችን ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል። የደህንነት ባለሞያዎችም በናይጄሪያ ደቡባዊ ምዕራብ ኦንዶ ክፍለ ግዛት የተካሄደው ጥቃት፣ በቅርቡ ወደ አገሪቱ ዋና ከተማ የሚስፋፋ የሽብርተኝነት ጥቃት ሊሆን ይችላል ሲሉ ሰግተዋል፡፡

በአቡጃ ወደሚገኘው ቤተክርስቲያን ለጸሎት የሚመጡ ምዕመናን ወደ ቤተክርስቲኒቱ ሲመጡ ወደ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት አንድ በአንድ እየተፈተሹ ይገባሉ፡፡ ፍተሻውን የሚያካሂዱት በግዛቱ የተመደቡ የጸጥታ ሰራተኞችና ፖሊሶች ናቸው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በናይጄሪያ ቤተክርስቲያናት ላይ በመካሄድ ላይ ከሚገኙት በርካታ ጥቃቶች አንጻር እርምጃዎቹአስፈላጊ መሆናቸውን የቤተክርስቲያን ባለሥልጣናት ይናገራሉ፡፡

የአቡጃ ፖሊሶች ወደ ቤተክርስቲያናት፣ መስጊዶችና ህዝባዊ ተቋማት ፖሊሶችን እያሰማሩ መሆኑን ያገልጻሉ፡፡ ይሁን እንጂ የጸጥታ ጥበቃ የሚደረግላቸው ሁሉም ህዝባዊ ተቋማት አይደሉም፡፡

“ሰሞኑን ሰዎች እንደ እብደት እያደረጋቸው ወደ ቤተክርስቲያናት እየሄዱ መተኮስ ጀምረዋል፡፡” የሚሉት የዶሚኒየን ቻፕል ኢንተርናሽናል ጳጳስ ጆን ፕሬይዝ ዳንኤል “ቤተክርስቲያናት የሚቃጣባቸውን ጥቃት ለመመከት ራሳቸውን ማስታጠቅ ያላባቸው ይመስለኛል፡፡ ያ ራስን መካለከል ነው፡፡ ራስ መካለከልን ደግሞ የሚቃወም ህግ ያለ አይመስለኝም፡፡” ብለዋል፡፡

እኤአ ሰኔ 5 በትልቁ የታጠቁ ሰዎች በደቡብ ምዕራብ ናይጄሪያ ኦዎ ከተማ የምትገኘው ቅዱስ ፍራንሲስ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን በጠመንጃና ፈንጂዎች በማጥቃት 40 ምዕመናን ገድለዋል፡፡

ከጥቃቱ 88 ሰዎች በህይወት የተረፉ ቢሆንም ከፉኛ ቆስለዋል፡፡ አንዳንዶቹ ጥቃቱን ሲገልጹ “በማይታመን ደረጃ የሚዘገንን ድርጊት ነው” ብለውታል፡፡

ስቴፈን ቸክስ ኦኮንዬ የተባሉ ምዕመን “እንደዚያ ያለ ጥቃት ለ20 ደቂቃ ያህል ሲካሄድ አንድም ፖሊስ በአካባቢው አልነበረም፡፡ ያ ማለት በአገሪቱ ምንም ዓይነት ደህንነት የለም ማለት ነው፡፡ ደህንነትን ማረጋገጥ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራበት የሚያስፈልገው አንዱ ጉዳይ ነው፡፡” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የናይጄሪያ ባለሥልጣናት በምዕራብ አፍሪካ ክፍለ ግዛት የሚንቀሳቀሰውን እስላማዊ መንግሥት ወይም ኢስዋፕ ተብሎ የሚጠራውን ቡድን ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡ አንዳንዶቹ ግን ያ በጥድፊያ የተደረሰበት ድምዳሜ ነው ይላሉ፡፡

ባለሙያዎችም ሽብርተኝነት በናይጄሪያ እየተስፋፋ ነው በማለት ይናገራሉ፡፡

ባላፈው ሳምንት በሰሜን ካዱና ክፍለ ግዛት ታጣቂዎች በሁለት ቤተክርስቲያናት ላይ ጥቃት ሰንዝረው ሶስት ሰዎችን በመግደል በርካቶችን አግተው ወስደዋል፡፡

ባላፈው እሁድ ታጣቂዎች በካዳኑና ኤዶ ግዛቶች ባደረሱት የተለያየ ጥቃት ሁለት የካቶሊክ ቀሳውስትን ገድለዋል፡፡

የናይጄሪያ ክርስቲያን ማህበር ጥቃቱ ያሳሰበው መሆኑን ገልጾ ባለሥልጣናቱ ድርጊቱን የሚያስቆም ጥበቃ ባለማድረጋቸው ወቅሰውን አስምቷል፡፡ የቤተክርስቲያናት ኃላፊዎችም የደህንነት ጥበቃውን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል፡፡

የናይጄሪያ ክርስቲያን ማህበር ዋና ጸሀፊ ጆሴፍ ዳራሞላ “እንደ ተቋም በማናቸውም ምክንያት በማንም ይሁን ማን ... ወይም እንደዚያ ያለውን ጥቃት ካደረሱት ጋር አጥብቀን እንለያያለን፣ ቤተክስቲያናት በሙሉ ግን ስለደህንነታቸው ማሰብና መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ ከጎንህ የቆመው ሰው ተጠርጣሪ ነው፡፡” ይላሉ፡፡

የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃሙዱ ቡኻሪ እኤአ በ2015 ምርጫውን ባሸነፉበት ወቅት በአገሪቱ ያለውን የአለመረጋጋት ችግር ላይ እንደሚሰሩ ተናግረው ነበር፡፡

ሁለተኛው ዙር የሥልጣን ዘመናቸው በሚያበቃበት በዚህ ወቅት እንደ ኦዎ ባሉ አካባቢዎች እየተስፋፋ ያለው ጥቃት በሚቀጥለው ዓመት ምርጫ ዋነኛው መነጋገሪያ እንደሚሆን በእርግጠኝነት መገመት ይቻላል፡፡

XS
SM
MD
LG