በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በድርቅ ለተጠቃችው ሶማሊያ ትኩረት እንዲሰጥ ግሪንፊልድ ጠየቁ


በድርቅ ለተጠቃችው ሶማሊያ ትኩረት እንዲሰጥ ግሪንፊልድ ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:04 0:00

በድርቅ ምክኒያት ዜጎቿ ለረሃብ ለተጋለጡባት ሶማሊያ ለጋሾች ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ሰዎችን ከሞት እንዲታደጉ በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ጠየቁ።

ሶማሊያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ ሀገሮች ጉብኝት ያደረጉት ግሪንፊልድ፤ ካሁኑ አስፈላጊው ድጋፍ ካልተደረገ በሶማሊያ የተከሰተው የምግብ እጥረት የብዙዎችን ህይወት ሊቀጥፍ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ ርሃብን ለመከላከል ተጨማሪ 40 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እንደምትለግስ አምባሳደር ግሪንፊልድ ከጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል።

XS
SM
MD
LG