በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጦርነቱ 3.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት የውሀ መሰረተልማት መውደሙ ተገለፀ


በጦርነቱ 3.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት የውሀ መሰረተልማት መውደሙ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:54 0:00

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት 3.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት የውሀ መሰረተልማት መውደሙን የውሀ እና ኤነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ገለፁ፡፡ ከትግራይ እና ከአማራ ክልሎች ያነጋገርናቸው ነዋሪዎችም የውሀ ተቋማቱ በጦርነቱ በመውደማቸው ችግር መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ተቋማቱን ለመጠገን የአጭር እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ዶ/ር ሀብታሙ ገልፀዋል፡፡ አስተዳደራዊ መዋቅር ባለባቸው የአፋርና የአማራ ክልሎች ከውሀ ቢሮዎች ጋራ እየተሠራ እንደሆነ የተናገሩት ዶ/ር ሀብታሙ፣ በትግራይ ክልል ግን መዋቅሩ ስለሌለ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከማዕከል ባለሞያዎችን እየላከ የጥገና ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG