በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባለፉት ሦስት ወራት በዘራፊዎች የተጎዱ 482 ታካሚዎችን ማስተናገዱን አይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታወቀ


 ባለፉት ሦስት ወራት በዘራፊዎች የተጎዱ 482 ታካሚዎችን ማስተናገዱን አይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:25 0:00

ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ፍጻሜ በኋላ በትግራይ ክልል እንደተስፋፋ ከተገለጸው የዘራፊዎች ጥቃት ጋራ በተያያዘ፣ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ብቻ ለ482 ጉዳተኞች የሕክምና አገልግሎት መስጠቱን፣ የዓይደር ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ኣስታወቀ፡፡

ብዙዎቹ ዝርፊያዎች፣ ጨለማን ተገን አድርጎ ሰዎችን በደንጊያ በመፈንከትና በስለት በመውጋት የሚፈጸሙ መኾናቸውን የገለጸው ሆስፒታሉ፣ በየቀኑ ከሚያስተናግዳቸው ጉዳተኞች መብዛት የተነሣ ባለው ውስን የሕክምና ቁሳቁሶች እና የባለሞያዎች ቁጥር ላይ ጫና መፍጠሩን አመልክቷል፡፡

በዝርፊያ ወንጀል መስፋፋት ሰዎች ሠርተው ለመግባት እየተቸገሩ መኾናቸውን ያመነው የመቐለ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፣ መጠኑን ለመቀነስ በተደረገው ጥረት ግን “መሻሻል ታይቷል፤” ብሏል፡፡

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ አራት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ባለፈው ሰኔ ወር ባወጡት መግለጫ፣ በክልሉ ሥርዐተ አልበኝነት መንገሡን በመጥቀስ ጊዜያዊ አስተዳደሩን በድክመት መውቀሳቸው ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG