No media source currently available
በአምቦ ሊካሄድ የነበረው በመጫና ቱለማ ማኅበር ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ መከልከሉ እንዳስከፋቸው ተሳታፊዎች ገለፁ። ውይይቱን ያዘጋጀው የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ውይይቱ እንዳይካሄድ የተከለከለው አንድ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በመሆኑ ተሳታፊዎች በመጉላላታቸው ይቅርታ እጠይቃለሁ ብሏል። የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ስለጉዳዩ መረጃ የለኝም ብለዋል።