ዋሽንግተን —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ተሰባስበው ላለፉት ስድስት ሳምንታት የመሪነት ሥልጠና ከወሰዱ ወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ብሩህ ተስፋ ላላት አህጉር እድገት ወጣቶች ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል።
በትላንትናው እለት በዋሽንግተን ዲሲ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ የማንዴላ ዋሽንግተን የመሪነት መርኃ-ግብር ተሳታፊ ወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች ጋር ለረዥም ጊዜ ተወያይተዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።