በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቆሼ አካባቢ ለሚኖሩ እናቶች የስራ እድል የፈጠረችው "የቱባ ኢትዮጵያ ዲዛይን" መስራቿ ወጣት


Kidest Tesfaye Tuba Ethiopia Design
Kidest Tesfaye Tuba Ethiopia Design

ቅድስት ተስፋዬ የቱባ ኢትዮጵያ ዲዛይን መስራች እና ስራ አስኪያጅ ናት፡፡ ከዓመታት በፊት የቆሼ አካባቢ ተደርምሶ የፈጠረው ሰብዓዊ አደጋ አካባቢን ለመጠበቅ ተመልሶ በጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ነገሮች ላይ እንድትሰራ አድርጓታል፡፡ አሁን ከክርና ከቆዳ የተሰራ ቦርሳ ታመርታለች፡፡

የምታመርታቸው ቦርሳዎች ከክር እና በቆዳ የሚሰሩ ሲሆኑ ክሮቹ ሙሉ ለሙሉ በእጅ ነው የሚመረቱት፡፡ ይህ ስራ የሚሰራውም ነዋሪነታቸው በዛው በቆሼ አካባቢ በሆኑ ስራ አጥ እናቶች ነው፡፡ በአሁን ሰዓትም ለብዙ እናቶች በቤት ውስጥ ሰላሳ በመቶ ከሚጣሉ እቃዎች ሰባ በመቶ ደግሞ በጥሬ እቃ የሚሰራውን የክር ምርት የምሰለጥን ሲሆን ስላሳ አምስት የሚሆኑ ሴቶችም በቋሚነት አብረዋት ይሰራሉ፡፡

በቀጣይ 5 ዓመት ከ500 በላይ ለሚሆኑ ሴቶች የሙያ ስልጠና የመስጠት ህልም እንዳላት የምትናገረው ቅድስት ቦርሳ ከመሸጡ በላይ ትልቁ ስኬቴም "አብረውኝ የሚሰሩት ሴቶች ተጨማሪ የኑሮ መደጎሚያ ገቢ ማግኘታቸው እና ትንሽም ቢሆን የእኔ የሚሉት ነገር መኖሩ ነው" ትላለች፡፡ ትልቁ ስኬታቸው እንደሆነ የምትናገረው ቅድስት ይሄ ስራ እናቶች ማኅበራዊ ሕይወታቸው ሳይስተጓጎል የሚሰሩትም ነው ትላለች፡፡

ቆሼ አካባቢ ለሚኖሩ እናቶች የስራ እድል የፈጠረችው የ'ቱባ ኢትዮጵያ ዲዛይን' መስራቿ ወጣት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:23 0:00


XS
SM
MD
LG