No media source currently available
ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ምላሽ እቅድ ሪፖርት መሰረት ወደ 1.8 ሚሊየን የሚጠጉ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች አሉ፡፡ኢትዮጵያ ከሰሞኑ እነዚህን ተፈናቃዮች የተመለከተ የካምፓላ ስምምነት በመባል የሚታወቅ አህጉራዊ ውል ፈርማለች፡፡ ስለ ውሉ ምንነት እና ስላለው ፋይዳ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል ፟አቀባይ የሆኑት አቶ ክሱት ገብረ እግዚአብሔር ለአሜሪካን ድምጽ አስረድተዋል፡፡