በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ለሚያከናውነው ምርመራ አሜሪካ ድጋፍ እንድትሰጥ ሂዩማን ራይትስ ዋች ጠየቀ - ኤርትራ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱን ሪፖርት ተቃወመች


የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት የጦር ወንጀል እንደተፈጸመ እውቅና ከመስጠቱ ጎን ለጎን የተመድ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ለሚያከናውነው ሥራ ድጋፍ እንዲሰጥ ሂዩማን ራይትስ ዋች ጠየቀ።

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቱ ጥያቄውን ያቀረበው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዓለም ሀገሮችን የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት ላይ በሰሜን ኢትዮጵያ በተደረገው ጦርነት የተሳተፉ ሁሉም ወገኖች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ሲል ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው።

የኤርትራ መንግሥት በበኩሉ ሪፖርቱን ውድቅ አድርጎታል። የኤርትራ መንግሥት ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ በኤርትራ ላይ የቀረበው ውንጀላ "በመረጃ ያልተደገፈ እና ጭብጥ የሌለው ነው" ሲል ተቃውሞውን አሰምቷል።

የኤርትራ መንግሥት በመግለጫው “በኤርትራ ላይ የቀረበው ወንጀል እና ክስ የአሜሪካ አስተዳደር በኤርትራ ላይ የሚከተለው ኢፍትሃዊ የጥላቻ አቋም እና የማጠልሸት ተግባር ነው” ሲል የበኩሉን ክስ አሰምቷል።

የአሜሪካ ውሳኔ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦር ሰራዊት እንዲሁም የህወሃት ኃይሎች እና የአማራ ክልል አባላት የፈፀሟቸውን ጥቃቶች የሚያጠቃልል ሲሆን ብሊንከን "የጭካኔ ድርጊቶችን የፈፀሙ አካላት ተጠያቂ መሆን አለባቸው" ብለዋል።

ብሊንከን አክለው በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል በመፈፀም ከህወሃት በስተቀር ሦስቱን ተጠያቂ ሲያደርጉ በዘር ማጽዳት ተግባር ደግሞ የአማራ ልዩ ኃይልን ተጠያቂ አድርገዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ሪፖርት "ማስረጃ በሌለው ክስ እና ማስፈራራት ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር የተደረገ አሻጥር ነው" ያለው የኤርትራ መንግሥት የአሜሪካ መንግስት "ህጋዊ ካልሆነ ጣልቃ ገብነት እና ውንጀላ" እንዲታቀብ ጠይቋል። የኤርትራ፣ ኢትዮጵያ እና የቀጠናው ህዝቦች ችግሮቻቸውን በራሳቸው የመፍታት ሙሉ አቅም እንዳላቸውም አመልክቷል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG