በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ አራት ሕፃናት በውኃ ሙላት ተወሰዱ


 በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ አራት ሕፃናት በውኃ ሙላት ተወሰዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:30 0:00

በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ አስተዳደር፣ አራት ሴት ሕፃናት፣ ከባድ ዝናም ባስከተለው የውኃ ሙላት መወሰዳቸውን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የከተማው ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ ገዳቱ፣ በደራሽ ውኃው ከተወሰዱት አራት ሕፃናት፣ እስከ አሁን የሁለቱ አስከሬን መገኘቱን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

የአንዲቱ ሟች ሕፃን ወላጅ አባት አቶ ሙሉነህ ሻንቆ፣ ሌላዋ ልጃቸው እህቷ በደራሽ ውኃው ስትነጠቅ በማየቷ በከፍተኛ ሥነ ልቡናዊ ጉዳት ላይ እንደምትገኝ አመልክተዋል፡፡

ከጥቂት ቀናት በፊት የገባው የክረምቱ ወቅት፣ ከመደበኛው በላይ ዝናም የሚጥልበት መኾኑን የገለጸው የኢትዮጵያ ሜትዮሮሎጂ ተቋም፣ ኅብረተሰቡ የልጆቹን እንቅስቃሴ እንዲቆጣጠር አሳስቧል፡፡

XS
SM
MD
LG