በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጦር መሣሪያ ባለቤትነት ላይ የተሟሟቀው የአሜሪካ ንግግር


ይህ አጋጣሚ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትን በአደባባይ አስለቅሷል፤
ይህ አጋጣሚ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትን በአደባባይ አስለቅሷል፤



please wait

No media source currently available

0:00 0:13:31 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

... ዕድሜአቸው ስድስትና ሰባት ዓመት የሆነ ሃያ ሕፃናት ...
... ዕድሜአቸው ስድስትና ሰባት ዓመት የሆነ ሃያ ሕፃናት ...

የዩናይትድ ስቴትስ ሕገመንግሥት የነፃነት ቀንዲል ሆኖ ለሃገሮችና በሃገሮች ሁሉ እንደአርአያ ይነሣል፤ ይወደሣል፡፡

አሜሪካዊያኑም ከሕገመንግሥታቸው በላይ አንዳች ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ይገነዘባሉና ለሁሉም ችግሮቻቸው መፍትሔ፣ ለሁሉም ጥያቄዎቻቸው መልስ ከሕገመንግሥታቸው ይሻሉ፤ ያከብሩታል፤ ይወድዱትማል፡፡

በአውሮፓ አቆጣጠር ዲሴምበር 15 ቀን 1791 ዓ.ም የወጣው የሕገመንግሥቱ የመብቶች ድንጋጌ አሥር ማሻሻያዎች የሚጀምሩት መሠረታዊ በሆነው ሃሣብንና ዕምነትን የመያዝ ነፃነትና መብት ሲሆን ይህንን ነፃነት ሊጋፋ የሚችል አንዳችም ሕግ በሕግ አውጭው የተወካዮች ምክር ቤት እንዳይወጣም አንቀፁ አጥብቆ ይከለክላል፡፡ ሕጎች ሁሉ በአሜሪካ ሲወጡ እያንዳንዳቸው ከዚህ ነፃነት መከበር አኳያ ይፈተሻሉ፡፡
ሳንዲ ሁክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ሳንዲ ሁክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

ይህንን አውራ ማሻሻያ ወዲያው ተከትሎ የሰፈረው የመብቶች ድንጋጌ ሁለተኛው ማሻሻያ ሰዎች መሣሪያ የማግኘትና የመያዝ መብት እንዳላቸው ያረጋግጣል፡፡
...
...

...
...
...
...
ይህ ድንጋጌ ባለፈው ቅዳሜ ልክ 221 ዓመት ሊሞላው በዋዜማው ነበር የሃያ ዓመቱ ወጣት አዳም ላንዛ በከኔክቲከቱ የኒው ታውን ሳንዲ ሁክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዕድሜአቸው ስድስትና ሰባት ዓመት የሆነ ሃያ ሕፃናትን፣ መምህራንና የትምህርት ቤቱን ዳይሬክተር፣ እንዲሁም የገዛ እናቱንና የራሱንም ጨምሮ በጠቅላላው የሃያ ስምንት ሰው ሕይወት ያረገፈው፡፡
ፖሊስ ደርሶበት አዳም እራሱን ቀድሞ ባያጠፋ ኖሮ የበለጠ ሰው መፍጀት የማችል መሣሪያና ጥይት ይዞ እንደነበር ታውቋል፡፡
ብሔራዊ ኀዘን
ብሔራዊ ኀዘን

ይህ አጋጣሚ ወዲያው ንግግር ያደረጉትን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በአደባባይ አስለቅሷል፤ ብዙዎችን አስለቅሷል፡፡ ብዙዎች ውስጣቸው ደምቷል፤ ብዙዎች እስከዛሬም ያለቅሣሉ፡፡
“ብሔራዊ የነፍጥ ማኅበር” – National Rifle Association (NRA)
“ብሔራዊ የነፍጥ ማኅበር” – National Rifle Association (NRA)

ለሕገመንግሥቱ ሁለተኛ ማሻሻያ መከበር ቆምያለሁ የሚለውና ለወትሮው በብርቱ የሚሟገተው ከአራት ሚሊየን በላይ አባላት ያሉት “ብሔራዊ የነፍጥ ማኅበር” – National Rifle Association (NRA) አደጋው ከተፈጠረ ጀምሮ ድምፁን አጠፋፍቶ ቆይቶ ትናንት ማምሻውን መግለጫ ይዞ ወጥቷል፡፡ “… እንዲህ ዓይነቱ አጋጣሚ ዳግመኛ እንዳይፈጠር ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የሚያስችል አስተዋፅዖ ለማበርከት ኤንአርኤ ዝግጁ ነው ብሏል፡፡ አስተዋፅዖው ምን እንደሚሆን ግን በዝርዝር አልተናገረም፡፡

ቁጣቸውን በብሔራዊ የነፍጥ ማኅበር ላይ የሚገልፁ አሜሪካዊያን
ቁጣቸውን በብሔራዊ የነፍጥ ማኅበር ላይ የሚገልፁ አሜሪካዊያን
ለማንኛውም ግን ንግግሮቹ ከሃገሪቱ ርዕሠ-ብሔር እስከ ተራ ዜጋ በተናጠል፣ በቡድን፣ በመገናኛ ብዙኃን፣ በየአደባባዩ ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአንድ ሣምንት ባነሠ ጊዜ ዛሬ ለሦስተኛ ጊዜ ቀጥተኛ ንግግር አድርገዋል፡፡

‘መሣሪያ በመያዝና በባለቤትነት ነፃነት ላይ ገደብ ሊጣል ይገባል’ ለሚሉ ብዙ ተሟጋቾች የዓርቡ የኒው ታውን አጋጣሚ ነዳጅና አቅም የሰጣቸው ይመስላል፡፡ “ይህ አጋጣሚ አንዳች ተግባር ሣይፈፀምበት ቢያልፍ ለዋሽንግተን የሚቀራት ጠባሣ ይሆናል” ሲሉ ያስጠነቅቃሉ “ከቃላት ይልቅ ተግባር ተግባር ተግባር” እያሉ የሚጎተጉቱት፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
ይህ ችግር ለመሆኑ ከመብቶችና ከነፃነቶች ጋር እንዴት ይታይ ይሆን? በሌሎች ሃገሮች፣ በኢትዮጵያም ላይስ እንዲህ ዓይነት ሥጋት ይኖር ይሆን? አሜሪካን በውል የሚያውቋት፣ የመብቶችና የነፃነት ተሟጋቹና ነባሩ ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “የነፃነት ውጤት ነው” ይሉታል፡፡ የኒው ታውኑ አጋጣሚ በእጅጉ እንዳሣዘናቸውና አሜሪካዊያንም እጅግ የዋኆችና ደጎች መሆናቸውን እንደሚያውቁ የገለፁት ፕሮፌሰር መስፍን ይህ ኅብረተሰብ ለዚህ ችግር መፍትሔ ያገኝለታል ብለው እንደሚያምኑም አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያን በተመለከተ እንዲህ ዓይነቱ የተናጠል የወንጀልና የጥፋት አድራጎት “ጠብመንጃ የያዘ፣ የተራበ ወታደር ዳቦ ሲለምን በታየባት ሃገር” ውስጥ ይፈፀማል የሚል ሃሣብ ለጊዜው እንደሌላቸው ገልፀዋል፡፡ በጦር መሣሪያ ባለቤትነት ላይ ግን ቁጥጥር መደረግ አለበት ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

“ነፃነትና ዴሞክራሲ የሌሎችን ሕይወት፣ ነፃነትና ዴሞክራሲ ማጥፋት አይደለም” የሚሉ በፅናት የተነሱ ዜጎቿ በቆሙባት አሜሪካ ይህ የኒው ታውን ትምህርት ቤት አጋጣሚ ለአዲስ የጦር መሣሪያ ባለቤትነት ቁጥጥር እርምጃ መንገድ ይከፍት ይሆን? ይህ ዛሬ አደባባይና ጠረጴዛ ላይ ያለ ጥያቄ ነው…
... ዕድሜአቸው ስድስትና ሰባት ዓመት የሆነ ሃያ ሕፃናት ...
... ዕድሜአቸው ስድስትና ሰባት ዓመት የሆነ ሃያ ሕፃናት ...

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG